ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ

0
1242

ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10ሺ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡

በትላንትናው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከማህበረሰቡ የተሰጠውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ መርካቶ ውስጥ ጣና የገበያ ማዕከል ጎን በሚገኝ አድማስ ህንፃ ውስጥ፤ አዲሱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ በሚፃረር መልኩ ተከማችቶ የተገኘው ከ10ሺ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር በማዋል ጠቅላላ ምርመራ እያካሄደበት እንደሆነ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡

የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባሎቻችንም ድርሻም የጎላ እንደነበር ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በማሰራጨት ለሽብር አላማ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ የጦር መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ያሉት ሃላፊው ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እንደካሄደበት ነው ብለዋል፡፡

የሽብርተኛ ቡድኖችን ተልዕኮ ለመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህዝቡ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መመላከቱን ከክፍለ ከተማው ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here