መስከረም 22 እና 23 የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል በማስመልከት ውይይት እየተካሄደ ነው

0
708

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 22 እና 23/ 2014 የሚከበር ሲሆን በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በሰላምና አብሮነት እንዲከበር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አባ-ገዳዎች፣ ሃደ-ሲንቄዎች እና የአገር ሽማግሌዎች እየተወያዩ ይገኛሉ።

የኢሬቻ በዓል አከባበር የአብሮነት፣ የእርቅና የሰላም እሴቶችን ይዞ የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑም በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት እንደሚሰጥበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የኢሬቻ በዓል በርካታ ህዝብ የሚታደምበት ክብረ በዓል በመሆኑ የዘንድሮ በዓል በሰላም እና በአብሮነት በደመቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል መስከረም 22 የሚከበር ሲሆን፣ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 23/ 2014 በቢሾፍቱ እንደሚከበርም አስተባባሪው ጨምረው ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here