በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

Views: 119

ጥር 1/2012// በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 30/2012 ምሽት ላይ በኹለት ተማሪዎች መካከል በተከሰተ ፀብ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አየለ አዳቶ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። በተጠቀሰው ቀን በተፈጠረው ፀብ ህይወቱ ያለፈው የአንደኛ ዓመት ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አስከሬን ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ሚኒልክ የተላከ ሲሆን ምርመራ ተደርጎለትም ወደ ትውልድ አገሩ ወልደያ እንደተላከ ዘገባው ያትታል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ በኹለት ተማሪዎች ፀብ ምክንያት
የተከሰተው አለመረጋጋት የአንድን ተማሪ ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ፖሊስ ከግድያው ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተያያዥነት ያላቸውን
44 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ የማጣራት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። በተፈጠረው ክስተት የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ
በሐዘን ድባብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የመማር ማስተማሩ ሒደት ግን እንዳልተቋረጠ ተገልጾ፤ የፊታችን ሰኞ ጥር 4/2012 በጊቢው የመጀመሪያው
ወሰነ ትምህርት ፈተና እንደሚጀምርም ኃላፊው ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com