መዝገብ

Category: ማኅበረ ፖለቲካ

ብልፅግና እና ኢሕአዴግ አንድ ናቸው በዘፈን ምርጫቸው?

ኢሕአዴግ በውህደት ወደ ብልፅግና ፓርቲ ተቀይሯል። በዚህ አዲስ ፓርቲም አዳዲስ የተባሉ አሠራሮችና አካሔዶች የተነሱ ሲሆን፣ በአብዛኛው ‹አገር በቀል› የሚለው ሐረግም በብዛት ይሰማ ጀምሯል። ይህን የሚያነሱት ሙሉጌታ አያሌው፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሆነ ልማታዊ መንግሥት ወይም አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ እንዲሁም መደመር፤ ሊመዘኑ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያልደመሩት የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ጥያቄ

ሴቶች እንደ አገር በሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ብቻ ሳይሆን በመደበኛ እንቅስቃሴም ከቤት እስከ አደባባይ በሰላም ማጣት ውስጥ እንደሚኖሩ የሚጠቅሱት ሕሊና ብርሃኑ፤ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ከፍተኛ ጥቃቶችም በቸልታና በዝምታ እየታለፉ ስለመሆናቸው ይጠቅሳሉ። በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ደረጃ ትኩረት የተነፈገ ከመሆኑ በላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር…

የ‹ዲ ፋክቶ› መንግሥት 30ኛ ዓመት!

የ›ዲ ፋክቶ›ን ጽንሰ ሐሳብና ምንነት የሚጠቁሙት ግዛቸው አበበ፥ ልብ አልተባለም እንጂ ቀድሞም በኢትዮጵያ ይልቁንም በትግራይ ክልልና በሕወሓት አገዛዝ የ‹ዲ ፋክቶ› መንግሥት ባህርያት ይታዩ ነበር ይላሉ። እንደውም ሠላሳ ዓመት ሞልቶታል ሲሉ ይጠቅሳሉ። አሁን ላይ ስለ መገንጠልና መለየት እንዲሁም ስለ ‹ዲ ፋክቶ…

ከአንድ ዓይነት ተግባር የተለየ ውጤት እየጠበቅን ይሆን?

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየእለቱ ማለዳ ላይ በሚቀርብ የትራፊክ አደጋ መረጃዎች ላይ በርካታ ቀላልና ከባድ አደጋዎች እንደሚደርሱ ይነገራል። ከሚደርሰው የንብረት ውድመትና ኪሳራ ውጪ የብዙ ሰዎች ሕይወትም በአሰቃቂና አሳዛኝ ሁኔታ ያልፋል። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ጉዳዩን ልብ ብሎ ‹እንደርሳለን› የሚል ንቅናቄ በኅዳር ወር ያዘጋጀ…

ለተሻለ ነገ ብንሠራስ?

ሳምንቱ ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኀን እንዲሁም በዓለም ትላልቅ በሚባሉ መድረኮች ላይ ሥሟ በተደጋጋሚና በትልቅነት የተነሳበት ነው። ቤተልሔም ነጋሽ ይህን ክስተት መነሻ አድርገው ይልቁንም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በኦስሎ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን መቀበላቸውን ተከትሎ፣ በዓለም ፊት የተገለጠውን የኢትዮጵያን ክብር አንስተዋል።…

ብልጽግና ፓርቲ ስለሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ምን ይላል?

በኢትዮጵያ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከሠለጠኑት አገራት ሳይቀር የቀደመ ታሪክ አለው የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፣ ተሳትፎውን በየዘመኑ ምን መልክ እንደነበራው በጥቂቱ በማቃኘት ይጀምራሉ። ኢሕአዴግ በአባላት ፓርቲዎቹ ውህደት (ከሕወሓት በቀር) የመሠረተውን ብልጽግና ፓርቲ ረቂቅ መመሪያ ደንብንም ከሴቶች ተሳትፎ አንጻር በመቃኘት ይተቻሉ። ይልቁንም ረቂቁ…

በአስገድዶ መድፈር ጉዳይ ለምን ቆሞ ተመልካቾች ሆንን?

እስከ ኅዳር 30 የሚቆየውንና በአገራችን ለ14ኛ ጊዜ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ የሚካሔደውን የ16 ቀና ንቅናቄ በማንሳት የሚጀምሩት ቤተልሔም ነጋሽ፤ አስገድዶ መድፈርና የተለያዩ ጥቃቶች ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቢደርሱም አሁንም የማይነገሩና በዝምታ የታለፉ ጥቃቶችና የሴቶች ታሪኮች እንዳሉ ያነሳሉ። በተለይም የደረሰባቸውን…

ትንንሽ ድሎችን ለማስቀጠል

ባለፈው ሳምንት በመገናኛ ብዙኀንና ማኅበራዊ ገጾ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ከነበሩ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የተሰማውን ዜና መዝዘው ያወጡት ቤተልሔም ነጋሽ፤ የወር አበባ የንፅህና መጠበቂያ ምርት የህከምና ቁሳቁስ አካል ሆኖ የመካተቱን ነገር አውስተዋል። እዚህ ውጤት ላይ ለመድረስም የብዙዎች ድምጽና ቅስቀሳ እንደነበር በማንሳት…

ላል-ይበላ – ስሙና እውነቱ

ቤተልሔም ነጋሽ በሥራ አጋጣሚ በፓሪስ በሚካሔደው የሰላም ፎረም ላይ በተዘጋጀ “ላሊበላ የባህል- ለሰላም ፕሮጀክት” የተሰኘ ፕሮጀክት የተነሳው የላሊበላን ነገር መለስ ብለው ወደ ላሊበላ ያደረጉትን ጉዞ እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል። በዚህም ላሊበላ ስላለው ገናና ስምና የታሪክ ስፍራ አንጻር ስላልተሰጠው ትኩረት ከነበራቸው ቆይታ ያጋጠማቸውን…

አስገድዶ መድፈር በሕክምና ቦታዎች ለፈውስ ሔዶ ሌላ ህመም?

ቤተልሔም ነጋሽ በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚሔዱ ሴቶች የሚያጋጥማቸውን የመደፈር አደጋ አንድ የፍርድ ውሳኔ የተሰጠበትን የፍርድ ሒደት (‘ኬዝ’) እንደማሳያ በማድረግ አቅርበዋል። ከዚሁ ርዕስ ጋር በተያያዘ አንድ በሕፃናትና ሴቶች ጥቃት ላይ ከሚሠራ የፖሊስ ባልደረባ ያገኙትን የፍርድ ቤት ውሰኔ መረጃ…

“እናት እውነት…” ለልደት ካርድ አይሠራም?

ቤተልሔም ነጋሽ በተለያየ ወቅት የኹለት ልጆቻቸውን የልደት ምስክር ወረቀት ለማውጣት ያጋጠማቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ልዩነት መነሻ በማድርግ፥ የወሳኝ ኹነት፣ ምዝገባና ምስክር ወረቀት አሠጣጥ አስቸጋሪነትን አሳይተዋል። የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሕጉ ማሻሻል፤ አገልግሎቱም ፈጣን ማድረግ ይገባል ሲሉ ተችተዋል።    …

“ስሜ ለምን? ነው” ፤ የለምን ሲሳይ ግለ ታሪክ

ስሜ ለምን? ነው” – My Name Is Why በሚል ርዕስ ስመጥሩ ኢትዮ- ኢንግሊዛዊው ገጣሚ በራሱ ሕይወት ዙሪያ የጻፈውን፣ ለገበያ በዋለ በኹለተኛ ሳምንት ብዙ ቅጂዎች የተሸጡለት መጽሐፍ ሆኖ በኢንግሊዝ በሚታተመው ሰንዴይ ታይምስ ላይ የተመዘገበውን መጽሐፍ ያነበቡት ቤተልሔም ነጋሽ፣ እይታቸውን አካፍለዋል።  …

ሴቶችን ከጥቃት የመጠበቅ ቸልተኝነት

ሥልጣናቸውን ምሽግ አድርገው በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙና የፈጸሙ መኖራቸውን በመጥቀስ የሚጀምሩት ቤተልሔም ነጋሽ፤ በተለያዩ ማስፈራሪያዎች ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችም ሪፖርት ሳያደርጉ በዝምታ እንደሚቀሩ ያነሳሉ። መንግሥትም የሴቶችን ጉዳይ በተለያዩ ዘርፎች አደረግሁ የሚለው ከምልክትነት አላለፈም፤ ሴቶችን ከጥቃት በመጠበቅም እርምጃ እየወሰደ አይደለም ይላሉ።…

ብሔራዊ “አለመግባባት”

ቤተልሔም ነጋሽ ሰሞኑን በአንዳንድ ባለሥልጣናትና የመብት አራማጆች የተፈጠሩ እሰጣ ገባዎችንና ንትረኮችን እንዲሁም የተፈጠሩ ኩነቶችን በማንሳት ለእብደት እየዳረጉን ነው ሲሉ ያማርራሉ፤ መፍትሔውም መቆጨት ነው ሲሉም አመላክተዋል።     የሰሞኑን ዙሪያ መለስ ትርምስና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ጉዳዮች ችላ ሲባሉ ላየ፤ ከግራ ቀኝ…

ደብሊን፤ ጊነስ ቢራና የአየርላንዳውያን አበርክቶ

ቤተልሔም ነጋሽ ባለፈው ሳምንት የጀመሩትን የአየርላንድ ጉብኝት በዚህ ሳምንት ያጠቃልላሉ። የዚህኛው መጣጥፋቸው የሞሃር ገደሎችን፣ የጊነስ ቢራ ታሪክ ሥፍራ እንዲሁም መዘክራቸውን ከማስጎብኘታቸው ባሻገር ከአገሬው ወግ ጀባ ብለዋል።     (ክፍል ኹለት) ደህና ብራ ሆኖ ከርሞ አስተናጋጅ ጓደኛዬን ይህን አየር ጠባይ ነው…

የደብሊን ተረኮች – ከውስኪ ሙዚየም እስከ አራቱ ወንጌላት

ለዕረፍት ኹለት ሳምንታትን በአየርላንድ ያሳለፉት ቤተልሔም ነጋሽ፥ የአገሪቱ መስህብ ከሆኑት መካከል በተለይ ስለውስኪ ሙዚየም እና ስለታዋቂው ቡክ ኦፍ ኬልስ ኤግዚቢሽና ቤተመጻሕፍት በመጻፍ ተደራሲያንን የጉብኝታቸው ተቋዳሽ አድርገዋል።     ስትገዙት ሀብታም የሚያደርጋችሁ ብቸኛ ነገር ጉዞ ነው። “TRAVEL IS THE ONLY THING…

“ሰንበት ለሰው እንጂ፥ ሰው ለሰንበት አልተሠራም!”

መንግሥት ሕግ ወይም መመሪያ የማውጣት ተመክሮው ለማሠራት ሳይሆን ለማሰር፤ ለሰው ሳይሆን በሰው ላይ እንደነበር የሚተቹት ቤተልሔም ነጋሽ፥ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የወጣውንና በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የብዙዎች መነጋገሪያ የሆነውን የኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት (የኤታስ) አገልግሎት አሰጣጥ ለመወሰን…

“ራዕይ በሌለበት ተስፋ የለም”

አምና ከነበርንበት በባሰ ሁኔታ እንገኛለን የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፣ እንደሕዝብ መሥራት የነበረብንን የቤት ሥራ ባለመሥራታችን፣ ስንጀምረው ምናልባት ስለምንመኘው ውጤት እንጂ ስለአካሔዳችንና ስለሒደቱ፣ በሒደቱም ሊገጥመን ስለሚችለው እንቅፋትና ተግዳሮት ያንንም ለማለፍ ስለሚያስፈልገን ዝግጅት ባለመምከራችን የመጣ ነው ሲሉ ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል። በግልም ይሁን በመንግሥት በጋራ…

“የሴቶችን መብት ለማሳነስ ሕገ መንግሥቱን እስከመተው?”

ቤተልሔም ነጋሽ በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ረቂቅ” በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን መነሻ በማድረግ፥ ከሴት ተወዳዳሪዎች ጋር በተያያዘ የተካተተውን አንቀጽ አግባብነት የለውም ሲሉ ተችተዋል። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 35 የተዘረዘሩትን የሴቶች መብት አትንጠቁን ሲሉም…

ወሲብ ንግድ ወንጀል ሳይሆን – አንድ መልኩን መከልከል ይቻላል?

ቤተልሔም ነጋሽ ባለፈው ቅዳሜ፣ ነሐሴ 17 የአዲስ ማለዳ ዕትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴተኛ አዳሪነት፣ ልመናና ጎዳና ተዳዳሪነትን ለመከላለከል ያዘጋጀውን ረቂቅ ሕግ መሰረት በማድረግ በተለይ ሴተኛ አዳሪነትን በተመለከተ አንድ መጣጥፍ ማስነበባቸው ይታወሳል። ጽሑፉን በሚያዘጋጁበት ወቅት ረቂቅ ሕጉን ማግኘት ባለመቻላቸው የመገናኛ…

የወሲብ ንግድን በሕግ መከልከል ፤ የበሽታውን መንስዔ ትቶ ምልክቱን?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሲብ ንግድን፣ ልመናንና ጎዳና ተዳዳሪነትን የሚከለክል አዲስ ሕግ ለማውጣት ረቂቅ ማዘጋጀቱን መነሻ በማድረግ፥ ቤተልሔም ነጋሽ የወሲብ ንግድን በተመለከተ ሕጉ መነሻውን ሳይሆን ምልክቱን ለማከም የሚሞክር እንዳይሆን ሲሉ ያላቸውን ሥጋት አንጸባርቀዋል።     “የወሲብ ንግድ ፣ አስቀያሚ ማኅበራዊ…

የማስተማሪያ ቋንቋ ጉዳይ

ቤተልሔም ነጋሽ የአፍ መፍቻ ቋንቋን ትምህርት ለማስተማር ተግባራዊ የተደረገውን ፖሊሲ በተመለከተ የሐረሪ ክልልን እንደማሳያ ተጠቅመው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የተጠና ጥናትን ዋቢ አድርገው ፖሊሲው ከአተገባበሩ ጋር አልተጣጣመም ሲሉ መከራከሪያቸውን ተግዳሮት ካሏቸው ነጥቦች ጋር አቅርበዋል፤ ፖሊሲው ክለሳና ማሻሻያ ያስፈልገዋልም ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።…

ሚዲያና የሴቶች ነገር

መገናኛ ብዙኀን ማኅበረሰቡ ለሴቶች የሚሰጠው ቦታ፣ ደረጃና አመለካከት በአጠቃላይ አሉታዊ ጅምላ ፍረጃ ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተዛባ አመለካከት ሰለባ አድርጓቸዋል ሲሉ ኹለት የቴሌቪዥን መርሃ ግብሮችን ለአብነት የጠቀሱት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ይህንን በሚመለከት በተለይ በመገናኛ ብዙኀን ላይ መወሰድ ይገባቸዋል ያሉትን እርምጃዎችንም ጠቁመዋል። ባለፈው እሁድ…

ከሴት ሕፃን ልጅና ከችግኝ፡ የማን ሕይወት ይበልጣል?

ሴት ሕፃናትን “አስገድዶ” በመድፈር ወንጀል የፈጸሙ አንድ አዛውንትንና ችግኞችን በመንቀል በተከሰሰ ግለሰብ ላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈባቸውን ቅጣት በማነፃፀር ጽሑፋቸውን የሚጀምሩት ቤተልሔም ነጋሽ፥ የሴት ሕፃናትና ሴቶች ደኅንነት ለመንግሥት አንገብጋቢ አይደለም ሲሉ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። ሐሳባቸውንም ለማጠናከር አሳማኝ ያሉዋቸውን ማስረጃዎች ጠቃቅሰዋል። ገና ርዕሱን…

ረቂቅ የምርጫ ሕጉ እና ሴቶች “እኩል ውክልና ከሌለ ድምጽ አንሰጥም ብንልስ?

የምርጫ ረቂቅ ሕጉን መነሻ ያደረጉት ሩት ሰለሞን፥ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ እያደረገች ያለችውን ጅምር ጥረት በማድነቅ የሴቶችን መብቶች ለመጠበቅ በሕገ መንግሥቱ የተካተቱትም ሆነ አገሪቱ ፈርማ ያጸደቀቻቸውን ዓለም ዐቀፍ ስምምነቶች መከበር እንዳለባቸው ያሳስባሉ። ሩት ረቂቅ የምርጫ ሕጉ እነዚህን…

ማኅበራዊ ፍትሕ ስለማስፈን – የአዲስ አበባ ነፃ ዩኒፎርምና ደብተር ዘመቻ እንደማሳያ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ በቅርቡ ተማሪዎችን መመገብ፣ ደብተርና ዩኒፎርም በነፃ መስጠትን እንደ አንድ የማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈኛ መንገድ ማሳያነት የተጠቀሙት ቤተልሐየም ነጋሽ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደሃ ዜጎች መኖሪያ በሆነችው ኢትዮጵያ እነዚህ ተግባራት እንደመልካም ልምድ መወሰድ ይገባቸዋል ይላሉ። ይሁንና ማኅበራዊ…

ሞምባሳ፤ የኬንያዋ የባሕር ፈርጥ

ለሥራ በተለያዩ አገሮች የሚጓዙት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ገላጭ በሆነው ጽሁፋቸው የቱሪስቶች መናኸሪያ የሆነችውን የኬንያዋን የባሕር ዳርቻ ከተማ ሞምባሳን ያስቃኙናል፤ በጎ በጎውን ብቻ ሳይሆን ሥጋት ናቸው ያሏቸውንም ጉዳዮች ከትበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሞምባሳ ቀጥታ በረራ ያደርጋል። ኢቲ 322 ከዚህ…

“አንበሳው መጻፍ እስኪማር፤ ሁሉም ታሪክ አዳኙን ያወድሳል” የአፍሪካውያን አባባል

ኢትዮጵያ በዓለም ዐቀፍ ቋንቋ ብዙ ጻሕፍት ማፍራት ባለመቻሏ ሌሎች ለእኛ የሚኖራቸው ግምት የተሳሳተ እንደሆነ ቤተልሔም ነጋሽ በሥራ አጋጣሚ በተዘዋወሩባቸው የአፍሪካ አገራት መታዘባቸውን መነሻ በማድረግ የራሳችንን ታሪክ መጻፍ ካልቻልን ሌሎች በፈለጉት መንገድ ታሪካችንን እንደሚጽፉትም ማስረጃ በማጣቀስ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። በርግጥ ኹለት ኢትዮጵያውያን…

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ – የምንከፍለውን ዋጋ ለመቀነስ

በቅርቡ በአማራ ብሔራዊ ክልል የተካሔደውን “መፈንቅለ መንግሥት” መሰረት በማድረግ መንግሥት ተከታታይና ወቅታዊ መረጃ መስጠት አለመቻሉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲስፋፉ በማድረግ ወደ ብጥብጥና አለመረጋጋት ሊያመራ ይችላል የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ኮሽ ባለ ቁጥር ኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚዲያን መዝጋት እስከ መቼ መፍትሔ ይሆናል ሲሉም ይጠይቃሉ።…

የ“ፌሚኒዝም”ን ዓይነት የተሻለ ዓለም ለመፍጠር

“ፌምኒዝም” ከቃሉ እስከ ጽህሰ ሐሳቡ ብዙዎችን ያጨቃጭቃል። ቤተልሔም ነጋሽ ከቀላሉ የመዝገበ ቃላት ብያኔው በመነሳት በሴትና በወንድ እኩልነት ላይ ተመስርቶ የሴቶች መብት እንዲከበር የሚሠራ ንቅናቄ ሲሉ ይንደረደራሉ። ፌሚኒዝም ጎጂ ባሕልን ከመቃወም ባሻገር በኢትዮጵያ መሰረታዊ መብቶች መከበር ያስፈልጋል ሲሉ መከራከሪያ ሐሳብም ያቀርባሉ።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com