የእለት ዜና
 

ስለአዲስ ማለዳ

መግቢያ

አዲስ ማለዳ ሳምንታዊ የቅዳሜ ባለ 24 ገፅ ጋዜጣ ሲሆን የጋዜጣው ይዘት በዋናነት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዜና፣ ትንታኔና እና ቅኝት የሚቀርብበት የመገናኛ ብዙሃን ነው፡፡

ዓላማ እና ርዕይ

 • ዋና ዓላማ

በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሆነ ተፅእኖ ፈጣሪ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም መገንባት

 • ዝርዝር ዓላማዎች
 • ወቅታዊ መረጃ ማቅረብ
 • ትምህርት አዘል ስልጡን ውይይት/መድረክ መፍጠር
 • ዲሞክራሲያዊነት እንዲያብብ፣ የመብት ጠያቂነት እንዲጎለብት ብሎም ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዲዳብር መታገል
 • የዜጆች ድምፅ/ልሳን መሆን
 • ርዕይ

በኢትዮጵያ የአራተኛ መንግስት ሚናውን የሚወጣ ነፃ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ ብዙሃን መገናኛ መሆን

ዕሴቶች

 • ሀቀኝነት (factuality)
 • ምክንያታዊነት (rationality)
 • ብዝሃነት (pluralism)
 • ሥልጡንነት (civility)
 • ጨዋነት (ethics)
 • ሙያተኝነት (professionalism)

በጋዜጣው ላይ የሚወጡ የጽሑፎች ደረጃ መመዘኛ

 • ጉዳዩ እና ጥሬ ሀቅ (issue & fact)፡ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያለው ጥሬ ሃቅና አነጋጋሪው ጉዳይ ምንድን ነው የሚለውን ያመለክታል፡፡ ጥሬ ሀቅ በመረጃ የተደገፈ እውነታ ሲሆን ጉዳዩ ደግሞ ለመፃፍ ገፊ የሆነው ምክንያት ነው፡፡
 • ወጥነት (originality)፡ ጽሑፎቹ በሌሎች መገናኛ ብዙሃን/ መድረክ ያለተዳሰሱ ሃሰብ ማቅረብ እንዲሁም በመጣጠፎቹ ውስጥ የመነሻ ትንታኔና መደምደሚያ ሃሳቦች አለመበታተን
 • ሰውኛነት (personification)፡ አንድን/አንዲትን ባለታሪክ የጉዳዩ ባለታሪክ አድርጎ ማቅረብ
 • ቅርበት (proximity)፡ ከተደራሲው/ከጋዜጣው አንባቢ ጋር በስሜት ለመግባበባት መሞከር
 • አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ምንጮችን መጥቀስ (primary and secondary source)

የአዲስ ማለዳ ይዘት በዝርዘር

ሀ. ርዕሰ አንቀፅ

 • የሚፃፍበት ርዕስ በኤዲቶሪያል ውይይት ይወሰናል
 • ሐተታ ዘማለዳ ላይ ሊመሰረት ይችላል
 • አንድ ገፅ ሆኖ ከ 800 ቃላት ማነስ የለበትም

ለ.  ሐተታ ዘ ማለዳ

 • ወቅታዊና ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ላይ ያተኩራል
 • በአጠቃላይ በሁለት ገፅ ላይ ሆኖ ከ 1800-2200 ቃላት ይፃፋል
 • ከ 80 – 100 ቃላት ድረስ የያዘ ቅንጭብ መግቢያ(blurb) ይኖረዋል

ሐ. ዜና

 • ሁለት ዓይነት ዜና ይኖረዋል፡ አቦል ዜና እና ወፍ በረር ዜና

አቦል ዜና

 • በየዕትሙ ከአምስት ያላነሱ ትኩስ ወሬዎች ይኖራሉ
 • የዳራ መረጃ(background information) እንዲካተትባቸው ይደረጋል
 • እያንዳንዱ ዜና ከ500-600 ቃላት ይኖረዋል

ወፍ በረር ዜና

 • በየዕትሙ ከአምሰት ያላነሱ አጫጭር ወሬዎች ይስተናገዳሉ
 • እያንዳንዱ ዜና ከ100-150 ቃላት ይኖረዋል

መ. ዓውደ ሐሳብ

 • ወቅታዊ እና ከአዲስ ማለዳ ዕሴቶቻች ጋር የማይቃረን መሆን ይኖርበታል
 • ጸሐፍት በግብዣ ወይም ያለግብዣ ጽሑፍ ያቀርባሉ
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

ሠ. ምጣኔ ሀብት

 • በቋሚ አምደኛ የሚዘጋጅ ሆኖ ቢያንስ ሁለት አምደኞች በፈረቃ ይፅፉበታል
 • ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኩራል
 • በቀላል እና ግልፅ አጻጻፍ ይቀርባል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

ረ. ማሕበረሰብ

 • በቋሚ አምደኛ የሚዘጋጅ ሆኖ ቢያንስ ሁለት አምደኞች በፈረቃ ይፅፉበታል
 • ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኩራል
 • በቀላል እና ግልፅ አጻጻፍ ይቀርባል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

ሲቄ

 • በማሕበረሰብ ገፅ የቀኝ ጥግ ላይ በሴቶች ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያነጠነጥን ሆኖ በተለያዩ ሴቶች ብቻ የሚጻፍ የግል ምልከታ የሚቀርበበት
 • ጸሐፍት በግብዣ ወይም ያለግብዣ ጽሑፍ ያቀርባሉ
 • በአጠቃለይ ከ 350 ያልበለጡ ቃላት ይኖረዋል

ሰ. በታሪክ ዕይታ

 • በቋሚ አምደኛ የሚዘጋጅ ሆኖ ቢያንስ ሁለት አምደኞች በፈረቃ ይፅፉበታል
 • ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኩራል
 • በቀላል እና ግልፅ አጻጻፍ ይቀርባል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

ሸ. ባህልና ጥበብ

 • በዘጋቢዎች የሚዘጋጅ
 • ይዘቱ አጫጭር ዜና፣ ቃለ መጠይቅ እና ቅኝት ያካትታል
 • በአጠቃላይ ሁለት ገፆች ላይ ይኖረዋል

ቀ. የመጽሐፍት ቅኝት

 • በቋሚ አምደኛ የሚዘጋጅ ሆኖ ቢያንስ ሁለት አምደኞች በፈረቃ ይፅፉበታል
 • በቀላል እና ግልፅ አጻጻፍ ይቀርባል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

በ. አንደበት

 • ቋሚ አምድ ሲሆን ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በሳል እና ጥልቀት ያለው ቃለ ምልልስ ታዋቂ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ይደረግበታል
 • በአጠቃላይ በሁለት ገፅ ላይ ይኖረዋል

ተ. ዓለም አቀፍ

 • ዘጋቢዎችና አርታዒዎች ይሰሩታል
 • በአንድ ርዕስ ላይ የሚያጠነጥን ወቅታዊ ዜና ትንታኔ ይኖረዋል
 • ከአምስት ያልበለጡ አጫጭር ዓለም አቀፍ ወሬዎች ያካትታል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይኖረዋል

ቸ. ሕግ፣ ጤና፣ አካባቢ ጥበቃና ወቅታዊ

 • በየሳምንቱ ተለዋዋጭ አምድ ይሆናሉ
 • በቀላል እና ግልፅ አጻጻፍ ይቀርባል
 • በአጠቃላይ በአንድ ገፅ ላይ የሚያልቅ ሆኖ ከ 1000-1200 ቃላት ይፃፋል

ኘ. ማረፊያ

 • አንድ ቋሚ አምድ ሆኖ ለአንባቢዎች ይዘጋጃል
error: Content is protected !!