በእስር የቆዩ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ክስ ተቋረጠ

Views: 434

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግኑኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ፣ የአክሰስ ሪል ስቴት እና የዘመን ባንክ መስራች ኤርሚያስ አመልጋ እና የቀድሞው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ቢኒያም ተወልደ ክሳቸው መቋረጡን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዛሬ ከሰአት በሰጠው መግለጫ ላይም ባጠቃላይ 63 እስረኞች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑን ይፋ አድርጓል፡፡

መግለጫውን የሰጡት በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የድንበር ተሸጋሪ እና የተደራጁ ወንጀሎች ክፍል ሃላፊ ፍቃዱ ለክሱ መቋረጥ የጤና ሁኔታ እና የፈፀሙት ወንጀል ከግምት ውስጥ መግባቱን ገልፀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com