ዮሃንስ ቧያሌው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

Views: 450

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት ሹመት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር የነበሩትን ዮሃንስ ቧያሌውን የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

እንዲሁም አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡

የሁለቱም አመራሮች ሹመት ከጥር 14 ጀምሮ የፀና መሆኑን ጽህፈት ቤቱ የገለፀ ሲሆን ዮሃንስ ቧያሌው ግን የክልሉ ምክር ቤት ከምክትል ርእሰ መስተዳድርነት ያነሳቸው ለአካዳሚው ተሾመዋል ከተባሉበት ቀን ከ 26 ቀናት በኋላ የካቲት 10/2012 እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ዮሃንስ የስክ ጥሪ ብናደርግም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com