የዮሐንስ ቧያለው ሹመት እምቢኝ ማለት

Views: 143

የአማራ ክልል ምክር ቤት የካቲት 10/2012 ባደረገው አስቸኳይ ጉባዔ ላይ የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ላቀ አያሌው እና የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ ቧያለው፣ ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ገና ከጅምሩ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር።

‹‹ክልሉን ለቅቀው ወደ ፌዴራል እንዲሄዱ ማድረግ ተገቢ አይደለም። ለክልሉ በሚያስፈልጉበት ወቅት ላይ እንዲነሱ መደረጉ አግባብነት የለውም፣ በዚህ ሰዓት ክልሉን ማደራጀት እና እንዲጠናከር በማድረግ ፋንታ ወደ ፌደራል መላክ ክልሉን የአመራርነት መለማመጃ ከማድረግ የዘለለ ትርጉም የለውም›› ሲሉም የምክር ቤቱ አባላት ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር።

ይህን የሰሙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሰው ኃይል ስምሪቱ የፓርቲያቸው መሆኑን በመግለጽ፣ የዮሐንስ ቧያለው የፓርቲ ተልዕኮ እንጂ ጉዳዩ በምክር ቤቱ የማይታይ መሆኑን ገለጹ።

ቀጥለውም ሹመቱን የማጽደቅና አለማፅደቅ ሥልጣን የምክር ቤቱ ነው፤ የምክር ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ። ነገር ግን የሌሎች አካላት ተፅዕኖ እንዳለበት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉም ምላሽ መስጠታቸውን የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት መዘገቡም የሚታወስ ነው።

ከቀናት በኋላ ዮሐንስ የአማራ ብልፅግና ኃላፊነት ሥልጣናቸውን በመልቀቅ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚን በፕሬዝዳንትነት ከየካቲት 14/2012 ጀምሮ መሾማቸው እንደተነገራቸውም ተነገራቸው።

ከክልል ሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ፣ በፌደራል መንግሥት አዲስ ሥልጣን እንደሚሰጣቸው ሲጠበቁ የነበሩት ዮሐንስ፣ የካቲት 17 በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በወጣ መረጃ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይፋም ተደረገ።

ይህን ጊዜም የዮሐንስ ሹመት ተከትሎ በርካቶች መነጋገሪያ አጃንዳ አደርጓቸው ነበር። እንዴት ይህ ሹመት ተሰጣቸው ብለው የጠየቁም አልጠፉ።
ዮሐንስም ከአማራ መገናኛ ብዙኀን ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ ‹‹አሁን ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ የለም›› በማለት ሹመቱን አልቀበለውም ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህንን ተከትሎም ሐሳባቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ካጋሩት መካከልም፣ እንዴት አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ኣባል የተሰጠውን የሥራ ድርሻ አልቀበልም ይላል፣ ይህ በፓርቲዎቹ በኩል ያለውን ክፍተት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ያሉም ነበሩ።

እንደውም ገና ከጅምሩ ስለ ሹመታቸው የሰሙት ዮሐንስ፣ ይህንን ሹመት መቀበል እንደሌለባቸውና እንደውም ይህ የሚያሳየው ፓርቲቸው ለእርሳቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ተደጋጋሚ ሐሳቦች ሲንሸራሸር ሰንብቷል።

ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ የለም ብለው መናገራቸውም ትክክል መሆኑ እና ሐሳባቸውን የደገፉም ጥቂቶች አልነበሩም። ኃላፊነቱን ከመስጠት በፊት የተቋሙ ሥም ማጥራት እና እንደገና መገንባት የመጀመሪያ ሥራ መሆን ነበርት ሲሉ ሐሳባቸው ያጋሩ ነበሩ።

አንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤ ‹‹የዮሐንስ ሹመታቸውን ምን እንደሆነ ያላወቁት የምክር ቤቱ አማራን ወክሎ ፌዴራል ላይ መሥራታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው ብላቸሁ ነበር። ይህን ስትሰሙስ ምን ተሰማቸሁ?››

ቅጽ 2 ቁጥር 69 የካቲት 21 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com