10ቱ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ እድገት የተመዘገበባቸው መስኮት

Views: 499

ምንጭ፡ – – ብሔራዊ ባንክ (2018/19)

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መካከል ከላይ በሰንጠረዡ ላይ እንደተቀመጠው፣ 10ቱ ዘርፎች በቀዳሚነት እድገት እያሳዩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።

በባንኩ የዐስርቱ ዝርዝር መሠረት፣ ከፍተኛ እድገት ከተመዘገበባቸውና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከታየባው ዘርፎች መካከል በቀዳሚነት የሚገኘው የትራንስፖርት እና የኮምዩኒኬሽን መስክ ነው። ይህም 21 በመቶ እድገት የታየበት ሲሆን፣ የግንባታው ዘርፍ 15 በመቶ ድርሻ በመያዝ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጠቅላላ ዓመቱ 9 በመቶ እድገት ያስመዘገበበት በጀት ዓመት ነበር። ይህም ከቀደመው የ2017/18 በጀት ዓመት መሻሻልና እድገት አሳይቷል። እነዚህ ዐስር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችም ለዚሁ አገራው የኢኮኖሚ እድገት የየድርሻቸውን ያበረከቱ ናቸው።

በድምሩም 11 በመቶ እድገት በአገልግሎት ሰጪው ዘርፍ፣ 3.8 በመቶ በግብርና እንዲሁም 12.6 በመቶው ደግሞ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የታዩ ለውጦች ናቸው። የኢትዮጵያም ዓመታዊ ጥቅም ምርት 1.8 ትሪሊየን ብር ደርሷል።

ከዝርዝሩም ውስጥ ጤና እና ማኅበራዊ ሥራ ዘርፍ ከቀደሙ ዓመታ ላቅ ያለ እድገት የታየባቸው መስኮች መሆናቸውን ሪፖርቱ በማካተት ጠቅሷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 69 የካቲት 21 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com