የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነገ ጀምሮ ለ15 ቀናት ሊዘጉ ነው

Views: 176

 

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከኮሮና ስጋት ጋር በተያያዘ ከመጋቢት 10 እስከ 24 ድረስ  በከፊል እንደሚዘጉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መአዛ አሸናፊ ገለፁ።

በከፊል ለመዝጋት የታሰበውም ማሕበራዊ ቅርርብን ለመቀነስ እንደሆነም ፕሬዝዳንቷ ዛሬ መጋቢት 09/2012 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።

ፍርድ ቤት ቀጠሮ ያላቸው ሰዎች ቀጠሯቸው መች እንደሆነ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይላክላቸዋል ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com