የፋናው ጋዜጠኛ በኮቪድ19 ምክንያት ራሱን ለይቶ ማቆያ አስገባ
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ በኮቪድ19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በመሆኑ ከጤና ሚኒስቴር ትላንት ማምሻውን በተገለጸለት መሠረት ከዛሬ መጋቢት 11/2012 ከጠዋት ጀምሮ በመኖሪያ ቤቱ እራሱን ለይቶ ማቆየት ጀመረ።
ጋዜጠኛው ከአንድ ተራድኦ ድርጅት ጋር በነበረው የሥራ ግንኙነት ለበሽታው ሊጋጥ የሚችልበት ዕድል እንዳለ በመገመቱ ነው ራሱን እንዲለይ የተደረገ ነው ሲሉ በፋና ያሉ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ግለሰቡ ምንም ዓይነት የበሽተው ምልክት ያላሳየ እና እስከ ትናትናው እለት ድረስ በስራ ገበታው ላይ የቆየ ሲሆን ጋዜጠኛውን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም ለማግኘት አልቻልንም።