በጌዲዮ ከ 1 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ለ5 ቀን የሚቆይ ስብሰባ ዛሬ ይጀምራሉ

Views: 2378

 

 

በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 12 ወረዳዎች ስር ከሚገኙ 164 ቀበሌዎች የተወጣጡ 1640 ሰዎች በየወረዳቸው ከዛሬ መጋቢት 14/ 2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ የብልፅግና ፓርቲ የበታች አመራር ስልጠና ይጀምራሉ።

ይህ ስብሰባ በክልሉ ባሉ የተለያዩ ዞኖችም እንደሚካሄድ ምንጮቻችን ገልፃው ነገር ግን ከመንግስት እውቅና ውጪ ፓርቲው ያደርገዋል ብለው አንደማያምኑ ተናግረዋል።

‹‹ክልሉ በኮማንድ ፖስት ስር ያለ ሲሆን ማንኛውም አይነት ስብሰባ የሚመለከተው የፌደራል የፀጥታ ሃይል ነው። ስለዚህ የፌደራል መንግስቱ አውቆ እና አምኖበት የፈቀደው ነው ብለን ነው የምናምነው›› ሲሉ በዞኑ ያሉ መካከለኛ አመራር ተናግረዋል።

አዲስ ማለዳ በሶማሌ ክልል ባደረገቸው ማጣራት የገዢው ፓርቲ ስብሰባዎች ባይኖሩም ሌሎች በርካታ ስብሰባዎች ግን እንደቀጠሉ ናቸው።

አዲስ ማለዳ የብልፅግና ፓርቲ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ አወሉ አብዲን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com