አውስትራሊያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ ልታደርግ ነው

Views: 725

የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች ውጤታማ እንደሚሆኑ ከፍተኛ ተስፋ በተጣለባቸው ኹለት የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ላይ ሙከራ ማድረግ ጀምረዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
እነዚህ ክትባቶች የተሰሩት በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና በአሜሪካው ድርጅት ኢኖቪዮ ፋርማሱቲካል ነው። ክትባቶቹ የመጀመርያ ዙር ሙከራን አልፈው በእንስሳት ላይ እንዲሞከሩ ፍቃድ አግኝተዋል። ለዚህም የዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ሰጥቶታል። ከዚያ በኋላም ሙከራው ወደ ሰው እንዲሸጋገር ፍቃድ ያገኛል ማለት ነው ተብሏል።
የአውስትራሊያ ብሔራዊ የሳይንስ ኤጀንሲ ክትባቶቹ የሚሰሩ መሆናቸውን እና ሰዎች ቢጠቀሟቸው አደጋ የማያደርሱ መሆናቸውን ይወስናል፡፡
የመጀመሪያዊ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በሰዎች ላይ የተካሔደው ከወር በፊት በኤሜሪካ የነበር ሲሆን በእንስሳት ላይ መደረግ የነበረበትን ሙከራ አላደረገም ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ በዓለም የተለያዩ ቦታዎች የክትባቶች ሙከራ በሚያስገርም ፍጥነት እየተካሔደ ይገኛል፡፡ በእኛም አገር በዚህ ሳምንት የኮቪድ 19 በሽታ መድኃኒት ተሰርቶ በሙከራ ላይ እንደሚገኝ ከባሕል ሕክምና ባለሙያዋ ሐኪም አበበች ሽፈራሁ ጋር ሲሰራ የቆየው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com