አመልድ ኮሮናን ለመከላከል እቤት ለሚውሉ ሰዎች የምግብ ድጋፍ አደረገ

Views: 313

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) የኮረና ቫይረስን መስፋፋት ለመከላከል በተለዩ አካባቢዎች ሰዎች በቤት ውስጥ ሲቆዩ ሊገጥማቸው የሚችለውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ የሚውልና ወረርሽኙን በሚገባ ለመከላከል እንዲቻል የ2 ሚሊዮን ብር የምግብ አቅርቦት ማድረጉን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ አስታወቁ፡፡
አመልድ 626 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 250 ኩንታል ማካሮኒ እና 1 ሺህ ካርቶን ብስኩት ለአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ማስረከቡን አለማየሁ ዋሴ(ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት በገጠር አካባቢ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል በክልሉ መደበኛ የምግብ ዕደላ በሚደረግላቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመጪው ጊዚያት በአካባቢያቸውና በቤታቸው መቆየት ይችሉ ዘንድ የኹለት ወራት ራሽን በአንድ ጊዜ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ተናግዋል፡፡
በዚህ መሰረት ለ172 ሺህ 304 ሕዝብ ለኹለት ወራት እንዲሁም 84 ሺህ 25 ሕዝብ ደግሞ ለአንድ ወር የሚያገለግል 6 ሺህ 429 ሜትሪክ ቶን (64 ሺህ 295 ኩንታል) ስንዴ፣ 642.94 ሜትሪክ ቶን (6 ሺህ 429 ኩንታል) የአተር ክክ እና 1 ሺህ 928 ኩንታል ዘይት በማደያ ጣቢያዎቹ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ውስጥ በተፈጥሮ አደጋ በተለይ በዝናብ እጥረት፣ በጎርፍ፣ በሰብል ተባይ ድንገተኛ ችግር የገጠማቸውን ወገኖች ለመደገፍ በሰሜን ወሎ ዞን ለ138 ሺህ 480 ሕዝብ የሚሆን 4 ሺህ 154.4 ሜትሪክ ቶን ስንዴ፣ 415.4 ሜትሪክ ቶን የአተር ክክ እና 124.6 ሜትሪክ ቶን ዘይት እንዲሁም በዋግኽምራ ዞን ለ48 ሺህ 926 ህዝብ 1 ሺህ 353.24 ስንዴ፣ 135.32 ሜትሪክ ቶን የአተር ክክ፣ 40.6 ሜትሪክ ቶን ዘይት በቤተሰብ ደረጃ የእህል እርዳታ ለማድረስ ወደ ማደያ ጣቢያዎች እየተጓጓዘ እንደሚገኝና የአካል ርቀትን ተግባራዊ በማድረግ ለተጠቃሚ ወገኖች እየደረሰ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com