መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናፍርድ ቤቱ የኢቢሲ የኦሮምኛ ክፍል ሀላፊ በላቸው ጀቤሳ እና አለማየሁ ቂጢሶ ያቀረቡት...

ፍርድ ቤቱ የኢቢሲ የኦሮምኛ ክፍል ሀላፊ በላቸው ጀቤሳ እና አለማየሁ ቂጢሶ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ አደረገ

ዕረቡ ሚያዚያ 12 (አዲስ ማለዳ) በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የኦሮምኛ ክፍል ሀላፊ በላቸው ጀቤሳ እና አለማየሁ ቂጢሶ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ውድቅ አደረገ።

ተከሳሾቹ ላይ ዓቃቢ ህግ በመጋቢት 9 ቀን 2014 ከሸገር ውሃ አምራች ድርጅት ባለቤት የግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበል ሙስና ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የኦሮምኛ ክፍል ሀላፊ አለባቸው ጀቤሳ የቀረበበት ክስ ግልጸኝነት እንደሚጎለው ጠቅሶ ክሱ እንዲሻሻልለት ጠይቋል።

2ኛ ተከሳሽ በግል ሥራ የሚተዳደረው አለማየሁ ቂጢሶ ደግሞ የቀረበው የሙስና ክስ ተደራራቢ መሆኑን የወንጀል ተሳትፎ በዝርዝር አለመጠቀሱን አመላክቶ ክሱ እንዲሻሻልለት የክስ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር።

ከሳሽ ዓቃቢህጉ በመጋቢት 26 ቀን 2014 በሰጠው የተከሳሾች የክስ መቃወሚያ መልስ ላይ በክሱ በአዋጅ 881/2007 አንቀጽ 10(1) ላይ በስህተት ከገባው ንዑስ አንቀጽ ሀ በስተቀር ክሱ ግልጸኝነት እንደማይጎለው አብራርቷል።

በተጨማሪም የወንጀል ተሳትፎ በዝርዝር አልተካተተም ለሚለው የተከሳሾች መቃወሚያ ከውሀ አምራች ድርጅት ሀላፊ ግማሽ ሚሊዮን ብር በቼክና በጥሬ ብር መቀበላቸው በክሱ በዝርዝር መካተቱን ጠቅሶ በጽሁፍ መልስ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።

የተከሳሾቹን የክስ መቃወሚያና የዓቃቢህግን መልስን የመረመረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ክሱ እንዲሻሻል ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ክሱን እንዲሻሻል የሚስችል አደለም ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ፍርድ ቤቱም የተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለሚያዚያ 26 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች