10ቱ በአፍሪካ የተሻለ ብዛት ያለው ቬንትሌተር የሚገኝባቸው አገራት

Views: 533

ምንጭ፡- ኒውዮርክ ታይምስ (2020)

ኒውዮርክ ታይምስ ከሳምንት በፊት (ሚያዝያ 11) ያወጣው ሐዘን የቀላቀለ ዘገባ ፈገግታን ፈጥሮ ነበር። እንዲህ የሚል ነው፣ አሥራ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ደቡብ ሱዳን ከአምስት በላይ በምክትል ማዕረግ ፕሬዝዳንቶች ያሏት ሲሆን፣ ይህም በቁጥር አራት ከሆነው የቬንትሌተሮቿ ብዛት ይበልጣል። በተመሳሳይ ጥቂት በማይባሉ የአፍሪካ አገራት የቬንትሌተሮች ብዛት ዐሥር ለመድረስ እንኳ የታደለ አይደለም።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ሰቅዞ በያዘበት ጊዜ፣ የተፈራላት አፍሪካ ዱላዋ እስከ አሁን ክፉኛ ያረፈባት ባይሆንም፣ ባለነበት ሁኔታ እንኳ የቬንትሌተሮች እጥረት እንዳለ ነው። ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበውም ዐስር የአፍሪካ አገራት አንድም እንኳ ቬንትሌተር የሌላቸው አሉ።

ወረርሽኙ ምንም እንኳ በጤናው መስክ ብቃት ላይ ደርሰናል ያሉትን ሳይቀር መፈተኑ ባይቀርም፣ ለአፍሪካ ከተለያዩ አቅጣጫ የመጡ ድጋፎች የቬንትሌተሮቹን ቁጥር በተወሰነ ደረጃ ከፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያም ኒውዮርክ ታይምስ ባስቀመጠው ዝርዝር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቬንትሌተር ያላት ሆና የተመዘገበች ሲሆን፣ በዚህም ስሌት መሠረት አንድ ቬንትሌተር ለ194 ሺሕ 99 ሰዎች ይደርሳል ማለት ነው።

ዘገባው በአፍሪካ በእድገትም ሆነ በጤና መስክ መሻሻል ቀዳሚ በምትባለው ደቡብ አፍሪካ በርካታ ቬንትሌተሮች እንዳሉ ቢጠቅስም በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ በዝርዝር አላስቀመጠም።

ቅጽ 2 ቁጥር 78 ሚያዝያ 24 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com