የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በኮቪድ19 ምክንያት የከፋ ችግር ቢመጣ ለመቋቋም የሚያስችል ዝግጅት መኖሩን አስታወቀ

Views: 228

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል በማዋቀር በጥብቅ ክትትል እየተሰራ እንደሚገኝና የከፋ ችግር ቢመጣም ለመቋቋም የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን በድሬዳዋ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አንድ ዩኒቨርሲቲ እና አምስት ትምህርት ቤቶች ለማቆያ እንዲሁም አንድ ማከሚያ ሆስፒታል ተለይተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በሳቢያን ሆስፒታል 104 አልጋዎችን በማዘጋጀትና ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ከሚያዚያ 9/2012 ዓ.ም ጀምሮ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሲ/ር መስከረም አሰፋ ወደ ሆስፒታሉ ገብተው የነበሩ 6 ታማሚዎች ከቫይረሱ መዳናቸውን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

መደበኛ የጤና አገልግሎቶችን አስመልክተው ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በሰጡት አስተያየት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ የሚገመግም ቡድን በማዋቀር በየተቋማቱ ምልከታና ዳሰሳ በማድረግ አስፈላጊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተቋማቱ በቦታ ጥበት ምክንያት ርቀት ያለመጠበቅ ችግርን ለመከላከል ድንኳኖችን በመትከል ጭምር እየተጠቀሙ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል ሲል የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com