በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር በዕድሜ ዝርዝር ተከፋፍለው ተገለፁ

Views: 121

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መገኘቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር በዕድሜ ዘርዝሮ ከፋፍሎ አስቀምጧል።

በዚህም መሰረት
ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆነ 1 ሰው፣ ከ5 ዓመትና ከዚያ በላይ 7 ሰዎች፣ ከ15 አስከ 24 ዓመት 91 ሰዎች፣ከ25 እስከ 34 ዓመት 75 ሰዎች፣ ከ35 እስከ 44 ዓመት 43 ሰዎች፣ከ45 እስከ 59 ዓመት ዕድሜ ያላቸው 26 ሰዎች እንዲሁም ከ60 በላይ የዕድሜ ክልል ያሉ 18 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል።

በአጠቃላይም 261 ሰዎች ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኘባቸው ኢኒስቲዩቱ አስታውቋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com