መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ

Views: 140

መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በሰአት እስከ 30 ሺህ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው ተርሚናል ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ እንደሚሆን ተገልጿል።

የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና የመንገደኞች መተላለፊያ ድልድይ እንዲሁም ባለ ስምንት ወለል ህንፃም የሚያካትት ሲሆን በአካባቢውን የሚታየውን መጨናነቅ በመቀነስ በኩልና የህዝብ ትራንስፖርትን በማዘመን በኩል የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ከንቲባ ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።

Posted by Takele Uma Banti on Wednesday, May 13, 2020

Posted by Takele Uma Banti on Wednesday, May 13, 2020

Posted by Takele Uma Banti on Wednesday, May 13, 2020

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com