በአጭር ጊዜ ለህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አስታወቀ

Views: 89

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውን የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ ወይዘሮ መእዛ አሸናፊ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ማከናወን አለመቻሉን ማስታወቁን ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥበት ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው፡፡

የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት ወይዘሮ መእዛ አሸናፊ በሂደቱ ዙሪያ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የቀረበውን የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

አሁን ላይም በስራ ላይ ያሉ 10 የጉባኤው አባላትን ይዞ በህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄው ዙሪያ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጉዳዩ የህገ መንግስት ትርጓሜ የሚያስፈልገው መሆኑ ይመረምራል ያሉት ወይዘሮ መአዛ፥ ትርጓሜ የሚሰጠው ጥያቄም ከሆነ የውሳኔ ሀሳብ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረባል ብለዋል።

በነገው እለትም ከህግ ባለሞያዎች ጋር ለህዝብ የሚተላለፍ ውይይት ይደረጋል ማለታቸውን የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com