በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥር 36.5 ሚሊዮን መድረሱ ተገለፀ

Views: 49

በአሜሪካ በባለፈው ሳምንት ብቻ 2.98 ሚሊዮን ሰዎች ስራ ማጣታቸውን ተከትሎ፣ ወረርሽኙ ከተነሳበት እለት ጀምሮ ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥርን ወደ 36.5 ሚሊዮን አድርሶታል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ እየተጠቃች ባለችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንዲሁም የሟች ቁጥር ከአለም ቀዳሚ ያደረጋት ሲሆን የምጣኔ ኃብቱም ጫና በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል።

በዚህም የተነሳ ስራቸውን ያጡ ሰዎችም የመንግሥትን እርዳታ በመሻት ድጎማ እንዲደረግላቸው የተለያዩ ቅፆችንም በመሙላት ላይ ናቸው።

ምንም እንኳን የስራ አጡ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቢያሻቅብም ወረርሽኙ ከተከሰተበት ከሁለት ወራት በፊት ጋር ሲነፃፀር በባለፉት ሳምንታት መቀነስ ማሳየቱን የአሜሪካ የሰራተኞች ዘርፍ አስታውቋል።

በባለፈው ወር 20.5 ሚሊዮን ስራ አጦች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም የስራ አጡን ቁጥር ወደ 14.7 በመቶ እንዳሻቀበው ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com