በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሀገራዊ የሎጀስትክስ ሥራ እንዳይስተጓጎል በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረስ

Views: 72

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ ከጅቡቲ መንግስት ጋር በቪዲዮ (virtual meeting) ባደረጉት ዉይይት የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል የሎጀስትክስ ሥርዓቱም ሳይተጓጎል በሚሄድበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል፡፡

በዚህ በዉይይታቸዉም የሀገራችንን የገቢና የወጪ ንግድ በዋናነት ከጅቡቲ ወደብ የሚከናወን በመሆኑ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ በጋር በማድረግ በሁለቱም ሀገራት ቫይረሱ እንዳይስፋፋ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት በማድረግ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በሌላ በኩል መጨናነቅን ለማስቀረት በቀጣይ የወደብ አመራጭን ለማስፋትና የሎጀስትክስ ወጪና ጊዜን ለመቆጠብ ታስቦ ከዚህ በፊት የተገነባዉን የታጁራ ወደብ መጠቀም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለዉ በዉይይቱ የተነሳ ሲሆን ከሁለቱም ሀገራት የጋራ ታክስ ፎርስ አቋቁመዋል፡፡

በመሆኑም ሁለቱም ሀገራት በቀጣይ በትኩረት በሚሰሩ ተግባራት ላይ የሥራ ክፍፍል በማድረግ እና የታጁራ ወደብን በአማራጭነት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታና የወደቡን አገልግሎት ማስጀመር ላይ አስፈላጊ የሆኑ የወደብ ፋሲሊትን ለማማላትና የጉሙሩክ አሰራር እንዲዘረጋ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ለማስጀመር የጋራ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ በዉይይቱ የሁለቱም ሀገራት የትራንስፖርት ዘርፍ አመራር አካላት መሳተፋቸዉ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com