ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ 15 ሰዎች የካሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ

Views: 117

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው 3707 የላብራቶሪ ምርመራ 15  ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ሚኒስተሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኛባቸው የተረጋገጠው 15ቱም ሰዎች ወንድ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ17 እስከ 38 መሆኑ ታውቋል፡፡

እነዚህም ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 8ቱ ከአዲስ አበባ፣ 2ቱ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል (ጉባ ለይቶ ማቆያ)፣ አንድ ሰው ከአፋር ክልል (መተማ ለይቶ ማቆያ) እንዲሁም 3ቱ ከሶማሊሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) የነበሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 287 ደርሷል፡፡

በተጨማሪም በትናንት እለት 4 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 መድረሱም ከሚኒስትሯ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com