የተባበሩት መንግሥታት 10 ሺህ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን አስታወቀ

Views: 58

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ወደ 10ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው መመለሱን ገለፀ፡፡

ከእነዚህም 10ሺህ የሚጠጉ ሰነድ አልባ ስደተኞች ውስጥ አብዛኛቹ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደሆኑም ተገልጿል ።

ከስደተኞቹ መካከል መጋቢት ወር ላይ ሞዛምቢክ ውስጥ ከሞት የተረፉት 11 ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።
11ዱ ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ በእቃ መጫኛ ከሌሎች ጋር ተጭነው እየሄዱ የነበረ ሲሆን 64ቱ ሲሞቱ እነርሱ ግን መትረፋቸው ይታወሳል።
ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ ለአስራ አራት ቀን በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን ረቡዕ እለት ከለይቶ ማቆያ ወጥተው ቤተሰቦቻቸውን መቀላቀላቸው ተሰምቷል ሲል የዘገበው ቢቢሲ አማርኛ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com