የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች እስር በአስቸኳይ እንዲቆም ኮሚሽኑ ጠየቀ

Views: 158

በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች እስር በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ።
የኢትዮጵያ ስብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም ባላቸው ነዋሪዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ተገቢነት የለውም ብለዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ደንቡ ማንኛውም ሰው በገበያ፣ በሱቆች፣ በትራንስፖርት አገልግሎት ባሉ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችና በሌሎች ሕዝብ በሚበዛባቸውና የአካል መራራቅን መጠበቅ በማይቻልባቸው አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዳለበት እንደሚደነግግ ዋና ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል።
ከዚህ ውጪ ግን በየትኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደረግ የዘፈቀደ እስር ከሕግ ውጭ ከመሆኑም በላይ፤ ለነገሩ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃና የታለመለትን ዓላማ የሚቃረን ነው በማለትም ዋና ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግንቦት 5/2012 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ያላደረጉ ከአንድ ሺሕ 300 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ በምክር መልቀቁን የገለጸ ቢሆንም፣ በቀጣዩ ቀን ግንቦት 6/2012 በአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ 300 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 80 ግንቦት 8 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com