በኢትዮጵያ በ24 ሰአት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

Views: 257

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 1775 የላብራቶሪ ምርመራ እስካሁን ድረስ ከተመዘገበው ቁጥር ከፍተኛ የተባለውን በ35 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 17ቱ ወንዶችና 18ቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እና ከ15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 352 አድርሶታል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ከእነሱም 1 የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ 23 በበሽታው ከያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 5 ሰዎች ምንም አይነት የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ሲሆኑ በተጨማሪም 1 ሰው ከ ኦሮሚያ ክልል የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ 4 ሰዎች ከሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ እንዲሁም 1 ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፤ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ 3 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 116 እንዳደረሰው ከሚኒስትሯ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እስካሁንም በአጠቃላይ 59,029 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com