ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ

Views: 56

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 3271 የላብራቶሪ ምርመራ 14 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 11 ወንድ እና 3 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ9 እስከ 68 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 365 እንዳደረሰው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 4 ሰዎች ከቫይረሱ በማገገማቸው በአጠቃላይ በሀገራችን ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱ ተገልጿል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በትናንትና እለት ቫይረሱ በምርመራ ተገኘባቸው ከተባሉት 35 ሰዎች ውስጥ 1 ግለሰብ ከዚህ በፊት ማለትም በግንቦት 9 በወጣው መግለጫ ሪፖርት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በድጋሚ በትናንትናው መግለጫ በመካተቱ የትናንቱ ሪፖርት 34 ሰዎች በሚል እንዲስተካከል በማለት ዶክተር ሊያ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com