ወጪ በሚደረግ ጥሬ ገንዘብ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ገደብ ተጣለ

Views: 97

የብሔራዊ ባንክ ገዚ ይናገር ደሴ ዛሬ ግንቦት 11 2012 በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሁሉም የንግድ ባንኮች በቀን የሚወጣው የጥሬ ገንዘብ መጠን ለግለሰብ 200ሺህ፣ ለኩባንያ ደግሞ 300ሺህ እንዲሆን መደረጉን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ግለሰብ አንድ ሚሊየን፣ ለኩባንያ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድረስ ብቻ ማውጣት እንደሚችል ተገልጿል።

መመሪያው በሁሉም ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የሚታዩ አንዳንድ አግባቦችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡

መመሪያው በቼክ፣ በሲፒኦ እና ሌሎች መንገዶች የሚካሔድ የገንዘብ ልውውጥ ላይ ገደብ አለመጣሉ ታውቋል።

በአዲሱ መመሪያ መሰረትም ባንኮች በየሳምንቱ ለብሄራዊ ባንክ ሪፖርትን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ከገደቡ በላይ የፈቀደ እና የሰጠ ባንክም የሰጠውን መጠን 25 % ወይንም አንድ አራተኛውን እንደሚቀጣም አዲስ ማለዳ ለማረጋገጥ ችላለች፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com