ደቡብ ኮሪያ ኮቪድ 19ን ለመዋጋት እንዲያስችል በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት የኮሪያ የጦር ዘማቾች 40 ሺህ የፊት ጭንብሎችን በድጋፍ መልክ ሰጠች

Views: 78

አዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ማክሰኞ እንደገለፀው የኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ኮሚቴ 70 ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ለ 132 የጦር ዘማቾች እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ አድርጓል፡፡

የልገሳውን ሥነ ስርዓት ላይ የኮሪያው አምባሳደር ሊም ሆን ሚን እንዳሉት ደቡብ ኮሪያ ሰላምና ነጻነቷን ለማስጠበቅ በግንባር ቀደምትነት የዘመቱላትን የኢትዮጵያ አርበኞችን መስዋእትነት ፈጽሞ አትረሳም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የጦር ዘማቾች ቡድን መሪ ደቡብ ኮሪያ ለቀድሞ ጦር ዘማቾች እና ቤተሰቦቻቸው ያበረከተችውን ልገሳና ለሌሎች የህክምና ድጋፍና ስኮላርሺፕ ፕሮግራሞች ሁሉ ምሰጋናቸውን አቅርበው ይህ የጠበቀ ግንኙነትም በቀጣይነት ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ኤምባሲው ጭምብሎቹን ለማድረስ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ የቀድሞ የኮሪያ ዘማች ቤቶችን ለመጎብኘት እና በየክፍለ-ሀገራቱም ላሉት ሰዎች በፖስታ ለመላክ ማቀዱም ታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com