ከ23 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

Views: 98

የገቢዎችና ጉምሩክ አመራሮችና ሠራተኞች በሁሉም የጉምሩክ ኬላና መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ቀንና ሌሊት በትጋት በመስራት ኮንትሮባንዲስቶችን ለመቆጣጠር ባደረጉት እንቅስቃሴ ከግንቦት 05-11/12 ዓ.ም ጀመሮ ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግምታዊ ዋጋቸው ከ23.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የገቢዎች ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

ሚኒስትር መስሪያቤቱ ዛሬ ግንቦት 13-11/2012 በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው የተያዙት የኮንሮባንድ ዕቃዎቹ በህገ-ወጥ መንገድና በቱርስት ስም የገቡ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ፣ አዳዲስ እና አሮጌ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሀኒቶች፣ ምግብና የምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ ሞባይሎች፣ ጫት፣ ሲጋራ እንዲሁም የዜጎቹን አእምሮ የሚጎዱ አደገኛ እፅና ሺሻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ብዛቱ 14,474 የቱርክ ሸጉጥ ጥይት እና 3 ስታር ሽጉጥ ከመተማ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለ ሰርባ ኬላ ፍተሻ ላይ ከፌደራል ፖሊስ አባላትና ከክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውል ማግረጉን ሚኒስትር መስሪያቤቱ አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙባቸው ቦታዎችም ድሬዳዋ፣ አዋሽ፣ ጅግጅጋ፣ ሀዋሳ፣ ሞያሌ፣ መቀሌ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባ እና ሌሎች የጉምሩክ ኬላና መቆጣጠሪያ ጣቢዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም  በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በቦሌ አየር መንገድ እና ሞጆ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በኩል የሚገቡት የዕቃዎችን ሠነድና ንግድ በማጭበርበር ለማስተላለፍ ቢሞክሩም በተደረገው ጥብቅ ፍተሻ ከ4.6 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ተጨማሪ ታክስና ግብር እንዲከፈል መደረጉም ታውቋል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት ለሀገርና ለህዝብ ተቆርቅሮ ስራቸውን በብቃት እያከናወኑ ላሉ የጉምሩክ ኬላና መቆጣጠርያ ጣቢያ ሠራተኞችና ተባባሪ አካላት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ ህዝብና ሀገርን በመጉዳት የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ኮንትሮባንዲስቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥሪዉን አስተላልፏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com