በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ ተጨማሪ 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ

Views: 76

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 3747 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 8 ወንድ እና 1 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከ 20 እስከ 49 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 2ቱ (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው) እንዲሁም 1 ሰው (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው)፣ 2 ሰዎች ከአፋር ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው)፣ 1 ሰው ከሶማሊያ ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው እና ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ያለ)፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው እና በማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያለ) እንዲሁም 2 ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ) መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 398 አድርሶታል፡፡

በተጨማሪም በትናንትናው እለት 1 ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ማገገሙን ተከትሎ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 123 መድረሱን ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

   
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com