1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ዛሬ ካልታየች እሁድ ተከብሮ የሚውል ተገለፀ

Views: 57

1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ እሁድ እለት ተከብሮ እንደሚውል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለመላው የእስልምና ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ በመልእክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የኢድ በዓል ሲያከብር የኮሮናቫይረስ የተከሰተበት ወቅት እንደመሆኑ በሽታው እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

በመሆኑም በእለቱ የኢድ ሰላትን ሁሉም በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል።

የኢድ አል-ፊጥር በዓል ሲከበርም የሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደተለመደው የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲያከብረውም ጥሪ አቅርበዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com