ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፈጠራ ሥራ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ለመደገፍ ጃክ ማ ባዘጋጁት ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

Views: 65

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮቪድ-19 ወቅት፣ የፈጠራ ሥራን ለመሥራት የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ብዙዎች ጠቃሚ ሐሳቦችን እያፈለቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጃክ ማ ተፅዕኖ አሳዳሪ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችን ለመደገፍ የአፍሪካን የቢዝነስ ጀግኖች የተሰኘ የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀታቸውን እንደተናገሩ ገልጸዋል።

ስለሆነም በፈጠራ ሥራ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ( www.africabusinessheroes.org/en/ ) ላይ በመግባትና የድረ ገጹን መረጃ አንብበው በማመልከት፣ በቀጣና ደረጃ የውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ጥሪ አቅርበዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com