ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

Views: 91

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ መልካ በሎ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

እንደ ኤፍ.ቢ.ሲ ዘገባ አደጋው የደረሰው በወረዳው ቶኩማ ጃላላ ካብራ ቀበሌ ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ 7 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡

በአደጋውም ከሞቱት ሰባት ሰዎች በተጨማሪ በንብረት እና በቤት እንስሳቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ገልፀዋል፡፡

በተፈጠረው ደራሽ ወንዝ ባስከተለው የተራራ መደርመስ ከሞቱት ሰዎች ውስጥም ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውንም ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com