በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን መግለጫ ተመልከረቶ የማጣራት ስራ መጀመሩን ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ

Views: 226

በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን መግለጫ መመልከታቸውን እንዲሁም በመግለፃው ላይ የማጣራት ስራም መጀመራቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አበቤ አስታወቁ።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ “ሰበዓዊ መብት የምናከብረው እና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችን እና ለፍትህ ስንል ነው” ብለዋል።

መግለጫውን የማጣራት ስራችንን አጠናቀን ምላሽ ለመስጠት በሂደት እያለን መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ ተሰራጭቷል ያሉት ወዘሮ አዳነች አሁንም ቢሆን ዘገባዉን ከይዘቱ፣ ከአካሄዱ፣ እንዲሁም የጉዳዩን እውነተኛነት እና ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው ብለዋል።

በዚህም የማጣራት ስራ በሚገኘውም ውጤት፣ ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ፣ መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን ሲሉም አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል ጥረት እንደሚደረግም ገልፀዋል።

በውይይቱ ሪፖርቱ እንዲስተካከል ለማደረግ ባይቻል እንኳን ለህዝቡና ለአለም እውነቱን እንዲያውቀዉ በመረጃ አስደግፈን እናሳያለን ሲሉ ተናግረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com