በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ፤ የ1 ሰው ህይወትም አልፏል

Views: 539

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,141 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እንዲሁም ተጨማሪ 1 ሰው በቫረሱ ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ይህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 አድርሶታል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 94 ወንድና 56 ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ 3 ዓመት እስከ 72 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከእነሱም ውስጥ 147 በዜግነት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 3ቱ ደግሞ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች

123 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣

1 ሰው ከአፋር ክልል፣

3 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣

2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣

13 ሰዎች ከአማራ ክልልና 6 ሰው ከሶማሌ ክልል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በቫይረሱ ምክንያት የተጨማሪ 1 ሰው (የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ) ሕይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 18 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል ተጨማሪ 4 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 250 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ቫይረሱ በሀገራችን እንደተገኘ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተደረጉት የላብራቶሪ ምርመራዎች ከተገኙ እለታዊ ቁጥሮች ጋር ሲነፃፀርም በዚህ ሁለት ሳምንታት የተመዘገቡት የታማሚዎች ቁጥር ከ300 መቶኛ በላይ ጭማሪን ማሳየቱን የጤና ሚንስትር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያስታወቁ ሲሆን ህብረተሰቡም ከምን ጊዜውም በላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የወረርሽኙን መዛመት ይገታ ዘንድ አሳስበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com