የኢራን መንግስት ዶናልድ ትራምፕን በቁጥጥር ስር ለማዋል የእስር ማዘዣ አወጣ

Views: 276

የኢራን መንግስት በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አልጀዚራ ሰበር ዜና ሲል ይዞ ወጥቷል።

የእስር ማዘዣው በፕሬዝዳንቱ ላይ እንዲወጣም ምክንያቱ ከወራት በፊት የኢራኑ ጄኔራል ቃሴም ሶሌማኒ ኢራቅ ውስጥ በትራምፕ ትዕዛዝ በድሮን አማካኝነት በተፈፀመ ጥቃት መገደላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

ጥቃቱ ከደረሰ ከአራት ቀናት በኋላ ፣ ቴህራን በአሜሪካ ወታደሮች በሚተዳደሩ ሁለት የኢራን ማዕከላት የተኩስ ጥቃትን በመሰንዘር የበቀል እርምጃ ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡ ይህ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግስታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በኢራን ላይ እንዲያራዘም ግፊት እንድታደርግ ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕንና በወቅቱ በጄኔራሉ ግድያ የተሳተፉ ከ30 የሚልቁ ሰዎችን አድኖ እንዲያቀርብላቸውም የኢራን ባለስልጣናት ኢንተርፖልን መጠየቃቸውም ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com