10ቱ በኢትዮጲያ ለህፃናት ደካማ የጤና አገልግሎት ያለባቸው ክልሎች

Views: 122

ምንጭ፡- UNICEF(2011 -2016)

ዩኒሴፍ በ2016 ቀደም ባሉት አምስት ዓመታት ያደረገውን የዳሰሳ ጥናት፣ ከሴንትራል እስታስቲክ ጋር በመሆን አሰናድቶ ባወጣው ዘገባ መሠረት ለሕጻናት በቂ ያልሆነና ያልተሟላ የጤና ስርአት ዝርጋታ ያለባቸው ብሎ በከተማ እና በገጠር ከፋፍሎ አስቀምጦታል።
ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በጤና ስርአት ዝርጋታ በገጠሩ ከፍል 72 በመቶ የሚሆነው ክፍተት እንዳለበት የተቀመጠ ሲሆን፣ በከተማው 35.7 ክፍተት እንዳለበት ዩኒሴፍ ያደረገው ይኸው ጥናት አመላክቷል።
በክልሎች እንደታየው ከሆነ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች የጤና ተቋማት ክፍተት ካለባቸው፤ የአንደኛ ደረጃውን ይዞ የተቀመጠው ከላይ ባለው ዝርዝር እንደተመላከተው የአፋር ክልል ሲሆን ካሉት ክልሎች አንጻር 81 በመቶ የሚሆነው የጤና ስርአት ክፍተት እንዳለበት ጥናቱ አሳይቷል።
ዩኒሴፍ የሚያደርገው ጥናት በአምስት ዓመት አንዴ የሚደረግ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 89 ሐምሌ 11 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com