10ቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰራተኞቻቸው ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፍሉ አገራት

Views: 299

ምንጭ፡ – What career is right for me ድረገጽ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሠራተኞች ለፍቶ አዳሪዎች ሲሆኑ፤ አገራትም ለእነዚህም ሠራተኞቻቸው ባላቸው አቅም ደሞዝ ይከፍላሉ። በአማካይ ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ ከፋይ ተብለው የተለዩ አገራት ሲኖሩ፣ ዋና ዋና የተባሉና በዐስርቱ ዝርዝር የተቀመጡት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት ናቸው።

በዚህም መሠረት ለሠራተኞቻቸው ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል አንደኛ ደረጃውን የያዘችው ሉዘምበርግ ስትሆን፣ በዚህች አገር ውስጥ 60,369 የአሜሪካን ዶላር አማካይ የሚከፈል የደሞዝ መጠን ነው። ይህቺ አገር የሕዝብ ቁጥሯ 576,249 ሲሆን በስፋትም ካሉት አገራት ውስጥ ትንሿ ናት። በመቀጠል ኹለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አገር አሜሪካ ስትሆን፣ አሜሪካ ለሠራተኞቿ ከምትከፍለው ከፍተኛ ዋጋ በአማካይ 58,714 የምትከፍል አገር ሆና ተቀምጣለች።

ቅጽ 2 ቁጥር 91 ሐምሌ 25 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com