የእለት ዜና

አማራ ክልል 153 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ 153 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ።
የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ይኸነው ዓለም በ2012 በጀት ዓመት ለ2 ሺሕ 214 ባለሀብቶች ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ2 ሺሕ 908 ባለሀብቶች ፍቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል። የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱት ባለሀብቶች ውስጥ 291 የሚሆኑት ወደ ሥራ የገቡ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 74 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አያይዘውም 47 ነጥብ 99 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባላሀብቶች ፍቃድ ለመስጠት ታቀዶ 153 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፍቃድ መሰጠቱን አስረድተዋል።
ከሥራ እድል ፈጠራ አኳያም ለ228 ሺሕ 42 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ395 ሺሕ 804 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርም ነው የገለጹት።
ለክልሉ ኢንቨስትመንት መጨመር የክልሉ ሰላምና ደኅንነት ካለፉት ዓመታት የተሻለ መሆን፣ የኅብረተሰቡ የመልማት ጥያቄ፣ የክልሉ ተወላጅ ባለሀብቶች የማልማት ፍላጎት ማደግ እንዲሁም የአመራሩ ቁርጠኝነት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!