የእለት ዜና

በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ 70/30 መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

በዘርፉ ዕድገት እንዳይመጣ መንግስት ማነቆ ሆኖብናል (አምራቾች)

በአገር ውስጥ ያለውን የብረት ፍጆታ ለማሟላት በሚደረገው እንቅስቃሴ 70 በመቶ የሚሆነውን ምርት ከአገር ውስጥ አምራቾች እንዲቀርብ እና ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ከውጪ እንዲገባ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ተደረገ።

10 ሚሊዮን ቶን አመታዊ ብረት ፍጆታ ያላት ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ 95 በመቶ የሚሆነውንም ምርት ከውጭ ታስገባ እንደነበርም የብረታ ብረት ኢንስቲትዩት ጥናት እና ፕላን ዳይሬክተር ጥላሁን አባይ ተናግረዋል።

ኢትዮጲያ የብረት መዓድን ለማውጣት የሚረዳ እናም (process ) ለማካሄድ አንድ ኢንዱስትሪ ለመገምባት 14 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ሲል የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲዉትይፋ አድርጓል።

በኢትዮጲያ ውስጥ ሊገነባ ታሰበው የብረት መአድን አውጥቶ በአገር ውስጥ ሒደቱን ለማስፈፀም የሚረዳ ፋብሪካ የብረት መአድን ( Iren ore product) የሚያወጣ አንድ ኢንዱስትሪ ለመገምባት 14 ቢሊዮን ብር እንደሚጠይቅ ተገልጿል። ከዚህም ባለፈ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት ምርቶች በውች ምንዛሬ ዕጥረት መስተጓጎላቸው በኢትዮጲያ ውስጥ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ኋላ ቀርነት እንዲኖር ያደረገው ምክንያት ነው ሲሉ የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲዉት የጥናት ዘርፍ ሃላፊ ጥላሁን ተናግረዋል።

በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በታቀደው ዕቅድ መሰረት ይሄን ችግር በተወሰነ ለመፍታት መታሰቡን እና ለዚህም ከዚህ ቀደም 95 በመቶ ከውጭ የሚገባውን ምርት ወደ 30 በመቶ ላመውረድ ታቅዷል ብለዋል።

ተቋሙ የ2012 እና ያለፉትን አስር አመት በገመገመት ጊዜ እንዳነሳው ከሆነ አስካን ካለው የኢትዮጲያ ካላት 10 ሚሊዮን ቶን ፍላጎት አስር በመቶ የሚሆነውን እንኳን ማሟላት እንዳልተቻለ የተነሳ ሲሆን ለዚህም ከፍተኛ ለሆነ ወጪ ዳርጓታል ተብሏል።

እንዴት ተደርጎ ወደ ምርት እና መዓድን ወደ ማውጣት መሄድ ይቻላል ተብሎ የሶስት ሃገር ካምፓኒዎች ጥናት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ጥናቱን ያከናወኑት የኢንግሊዝ ኩባኒያ ፣ ቻይና እና ሳውዝ ኮርያ ኩባኒያዎች ሲሆኑ በዚህም የቅድመ የአዋጪነት ጥናት ተካሂዶ የአዋጪነት ጥናት ገና አልተደረገም ተብሏል።

በጥናቱ መሰረትም ኢትዮጲያ አሁን ላይ ያሰበችውን 70 በመቶ በሀገር ውስጥ የማምረት ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ማስቀመጣቸውን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒሰውቲቲውት ገልፀዋል።

አንደኛው ጥሬ ዕቃውን ከውጪ ኢትዮጲያ አስመጥቶ ቀጣይ ሂደቶቹን በሀገር ውስጥ ማከናወን ሲሆን ፤ ሁለተናው ደግሞ ከመጀመርያው የብረት መዓድን አውጥቶ አዚሁ ሂደቱን ለማስፈፀም የሚረዳ ፋብሪካ ( Iren ore product) ተጠቅሞ ማውጣት እንደሆነ ተገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ውጥ ያሉ የኤከሌክትሮኒክስ እና ብረታብረት አምራች አቅራቢዎች እንዳነሱት ቅሬታ ደግሞ ዕድገቱ እንዳይመጣ ዋነኛው ማነቆ የሆነብን መንግስት ነው ብለዋል። ለዚህም እንደ ማሳያነት የተነሳው ነገር ባንኮች የግልም ይሁን የመንግስት የውጭ ምንዛሪ እጥረት በሀገሪቷ ላይ እንዳለ ብንረዳም ነገር ግን ሆን ተብሎ እኛ እንዳንጠቀም እያደረጉን ነው። በተለይ ደግሞ ዘርፍ ይመርጣሉ ተብሏል። ይሄ ደግሞ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒሰውቲቲውት ስር ለሚገኙ ዘርፎች እንዲዳከሙ እያደረገ ነው።

ሁለተኛው የተነሳው ቅሬታ ደግሞ በኢትዮጲያ ላይ ያለው የኃይል አቅርቦት እጥረት ለስራቸው እንቅፋት እምደሆነባቸው የተነሳ ሲሆን፤ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ይሄንን ሁሉ ተቋቁመን ሰርተን ነገር ግን መንግስት እራሱ ከዕኛ መጠቀም አይፈልግም ሲሉ ይናገራሉ ። አገር ውስጥ እያለ ከውጭ ማስገባትን ነው የሚመርጠው በማለት ወቅሰዋል። መንግስት ባለው መመርያ ከ500 ሺህ ብር በላይ ግዢ የሚፈፀም ከሆነ ከውጪ እንዲገባ ወይንም ከአገር ውስጥ እንዳይገዛ ይዘረዝራል። ቅድሚያ ይሄም መስታከል አለበትም ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 95 ነሐሴ 23 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!