የእለት ዜና

ለነዳጅ አከፋፋዮች የዱቤ ሽያጭ ሊቆም ነው

የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ደርጅት ለግል ኩባኒያዎች በዱቤ የሚያቀርበውን የነዳጅ አቅርቦት ለማስቀረት እየሰራ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናገረ።
ተቋሙ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገረው ከዚህ በኋላ የግል የነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች የሚፈልጉትን ያህል ነዳጅ ክፍያውን ፈፅመው መውሰድ እንዲገደዱ ሊደረግ መሆኑን እና ጥያቄም ለመንግስት ቀርቦ መልስ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላላ የነዳጅ አቅርቦቱ የዱቤ ስርዓት እንዲቀር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ ነው።ከዚህ ቀደም እዳ ያለባቸው የግል ኩባኒያዎችም እንዴት ወደ መስመሩ ይገባሉ የሚለው ላይም እየተሰራ ነው።

በኢትዮጲያ ነዳጅ አቅርቦት እና የዱቤ ሽያጩ ከሰባ አመት በላይ የነበረ እንደመሆኑ መጠን በዛው ልክ ችግሩም ቢሆን እየተሰራበት እንደነበርም አቅራቢ ድርጅቱ አስታውቋል ።
ይህንንም ተከትሎ ሁሉም ኩባኒያ ወደ ቀጥተኛ ንግድ እንዲገባ በማድረግ እንዴት እንሰራለን የሚለው ለመንግስት ጥያቄ ቀርቦ እየተጠበቀ መሆኑን ነው የተገለፀው።ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ እዳ የነበረባቸው አምስት የግል ኩባኒያዎችም አሁን እዳቸውን እየከፈሉ መሆኑንም የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ታደሰ ኃይለማሪያም ለአዲሰ ማለዳ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ እንዳሉት ከሆነ የግል አከፋፋዮች ከድርጅቱ በዱቤ ተረክበው ካከፋፈሉ በኋላ ነው ክፍያውን ሚፈፅሙልን ያሉት ስራ አስኪያጁ ነገር ግን እርሱን ስርዓት አቋርጦ የዱቤ ሽያጭ ማቆም ቀላል እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ቢሆንም ያለውን ማስተካከል አስፈለጊ በመሆኑ ምክንያት እና ይሄ ስርዓትም ከቀጠለ ዕዳቸውን የማይከፍሉ የግል ኩባኒያዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተቋሙን አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉም ታደሰ ጠቅሰዋል።ስለዚህም ጥያቄው ቀርቦ ከመንግስት ምላሽ እየተጠበቀ ነው በማለት ታደሰ ሀይለ ማርያም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደሚታወሰው ከአራት ወር በፊት የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነዳጅ ከሚሰጣቸው የግል ኩባኒዎች በዕዳ ምክንያት 200 ሚሊየን ብር ማጣቱ ተገልፆ ነበር። አምስት የግል ኩባኒያዎች 200 ሚሊየን ብር ዕዳ እንዳለባቸው እና በዚህም ተቋሙ እየተጎዳ መሆኑን ተናግው ነበር።

እነዚህም የግል ኩባኒያዎች ኤርታሌ፣ ብሌን ነዳጅ አከፋፋይ፣ ገነት ነዳጅ አከፋፋይን ጨምሮ አምስት የሚሆኑ ኩባንያዎችን ይፋ አድርጎ ነበር። አሁን እነዚህ የግል ኩባኒያዎች እዳቸውን እየከፈሉ መሆናቸው የተገለፀም ቢሆን ድርጅቱ ለረጅም ዘመናት ይሰራበት የነበረውን የዱቤ አገልግሎት ለማቆም ከመንግስት ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ሰምታለች።

ኢትዮጵያ በዓመት እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የምታስገባ ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገር ውስጥ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱም ጥናቶች ያመላክታሉ።

ከወራት በፊትም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ የነዳጅ ምርት በዓለምአቀፍ ደረጃ ዋጋው እጅግ በመውረዱ ኢትዮጵያ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ልታገኝ የምትችልበትን አጋጣሚ ሴፈስ ካፒታል ተሰኘ ዓለም አቀፍ አጥኚ ድርጅት መዘገቡም ይታወሳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 95 ነሐሴ 23 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!