የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ የህክምና ቁሳቁሶችን ለገንዘብ ሚኒስቴር ለገሰ

Views: 72

የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ የህክምና ቁሳቁሶችን ለገንዘብ ሚኒስቴር መለገሱ ተገለፀ፡፡ የቻይናው ሁለገብ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚውል በሚል የህክምና ቁሳቁሶችን ለገንዘብ ሚኒስቴር ለግሷል።

ኩባንያውን በመወከል የሁዋዌ የሰሜን አፍሪካ ቀጠና ሀላፊ ጂ ሁኢ እና የኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ቼን ሚንግሊያንግ የህክምና ቁሳቁሶችን ለፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ አስረክበዋል።

የተደረገው የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ 11 ሺህ የቀዶ ጥገና ጭምብሎች እና 55 የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘርን እንደሚያጠቃልል ተገልፀዋል፡፡
”በዚህ ወሳኝ የወረርሽኝ ወቅት ከሁዋዌ የተደረገውን የህክምና ቁሳቁስ ልገሳ እናደንቃለን” ሲሉም የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም “ይህ ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚሰማው ኩባንያ በንግድ ሥራውም ስኬት የሚያመጣ ነው” ብለዋል፡፡

ሁዋዌ ማህበራዊ ኃላፊነት ያለው ኩባንያ መሆኑን የገለፁት የሰሜን አፍሪካ ቀጠና ሀላፊ ጂ ሁኢ የአካባቢውን ህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

የኮኖና ቫይረስ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመዋጋት አስተዋፅዎ ካደረጉ ብዙ ኩባብያዎች መካከል ሁዋዌ አንደኛው መሆኑም ተጠቁሟል ። ምንጭ ኢዜአ

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com