ኮሚሽኑ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ሊያደርግ ነው

Views: 120

የጉምሩክ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ በመጪው 2013 ዓ.ም የወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ የተቋሙን የወረቀት አልባ ዲጂታል አገልግሎት ስራ መጀመርን አስመልክተው በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ኮሚሽኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

የተቋሙን የአሰራር ስርዓት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ በተለይም ኮሚሽኑ ራሱን ችሎ ከተደራጀ በኋላ የገቢና ወጪ ዕቃዎች ፍሰት ህግንና ስርዓትን ባከበረ መልኩ እና የሀገርን ገቢ ባማከለ መልኩ እንዲሳለጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማሻሻያ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ነው የገለፁት፡፡

የጉምሩክ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃን የሚያዘምንና በሰራተኞች ዘንድም ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን እንደሚያረጋግጥ ተስፋ የተጣለበት የወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት ስርዓት በቅርቡ እንደሚበሰር አክለዋል፡፡

ለሰራተኛውም በሲስተሙ ዙሪያ አስፈላጊው ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ከኮሚሽኑ ጋር በጥምረት የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የሚጀመረውን የወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎት በአግባቡና በተቀናጀ መልኩ እንዲገለገሉበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com