በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህከምና ለሚከታታሉ ዜጎች ወጪያቸው በመንግስት ይሸፈናል

Views: 85

በ2013 በጀት አመት የመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ምክትል ከንቲባዋ የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ የዘውዲቱ ሆስፒታል በጎበኙበት ወቅት ለይቶ በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህክምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ህሙማኑ በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት በማድረግ ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ መሆኑ ይታወቃል።
መንግስት ችግሩን ተረድቶ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያደርግ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ አዳነች ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በሶስት የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በሚኒሊክ፣ ዘውዲቱና ጳውሎስ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
በእነዚህ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ላሉ ዜጎች በ2013 በጀት አመት አመቱን ሙሉ ወጪያቸው እንደሚሸፈን ምክትል ከንቲባዋ አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ አስነብቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com