የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድን ወቀሰ

Views: 167

የኢትዮጲያ ህዝባዊ አብታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የምርጫ ቦርድ ህጉን ተከትሎ እየሰራ አይደለም ሲል ወቀሰ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች እኩል መሟላት ያለብንን አሟልተን ብንገኝም ምርጫ ቦርድ እራሱ ያወጣውን ህግ እየተገበረ አይደለም ሲሉ የኢህፓ ምክትል ሊቀ መንበር ሰለሞን ተሰማ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት የመጀመርያው የኢህአፓ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ታህሳስ 4 እና 5 2012 ጉባኤ ያካሔደ ሲሆን በአዲሱ ምርጫ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ህግ 1162/2011 መሰረት 10 ሺህ የሚሆን ፊርማ እና የአምስት መቶ አንድ የጉባኤ ተሳታፊዎች አሟልተን ነበር ነገር ግን ይሄን ባደረግን በ45 ቀን ውስጥ የሙሉ እውቅና ፈቃድ ሊሰጠን ሲገባ ከልክሎናል ብለዋል ፡፡

ምርጫ ቦርድ አንዳንድ ሰነዶችን ማስገቢያ ጊዜ ለሁሉም ድጋሚ ምዝገባ እና አንዳንድ መሟላት ሚገባቸውን እንዲያሟሉ የሰጠው የጊዜ ገደብ አስከ መጋቢት 3 ጊዜ ድረስ ነበር፡፡

ማሟላት የሚጠበቅብንን አሟልተን የሚፈለገውን የምዝገባ ቁጥር ከ 10 ሺህ በላይ ብናስገባም ሙሉ እውቅናውን ሳናገኝ ስምንት ወር ሞላን ብለዋል፡፡ ሙሉ እውቅና ማግኘት የሚቻለው በህጉ መሰረት የመጀመርያ ጉባኤ በተካሄደበት በአርባ አምስት ቀን ውስጥ ነው፡፡ በዚህም ህጉን ምርጫ ቦርድ እንዲያከብርልን ነው የምንፈልገው በማለት ጠይቀዋል፡፡

ሙሉ እውቅና ሳይሰጠን ለምን ቀረ ብለን ብንጠይቅም ፤ በኢትዮጲያ የተከሰተው ኮሮና ስጋት እና እርሱን ተከትሎ ደግሞ በወጣው አዋጅን ምክንያት መስራት አልቻልንም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነው ተናገሩት ፡፡

የቅድመ ዕውቅና ፈቃድ ኢህአፓ የተሰጠው ታህሳስ 2011 መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም መጋቢት 11 ሶስት ፅህፈት ቤቶችን በአዲስ አበባ፣ በደሴ እና በጎንደር መክፈታቸውን ይናገራሉ፡፡

ምርጫ ቦርድ እራሱ ያወጣውን ህግ እንዲያከብር እና ማክበርም ግዴታው ሆኖ ሳለ እሚጠበቅበትን ባለማሟላቱ እና ሙሉ እውቅና ባለማግኘታችን ምክንያት እያደረግነው ላለነው እንቅስቃሴ ከባድ ጫና እየተፈጠረብን ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
ዋናው እና ከባዱ ህዝቡ ውስጥ ገብተን እንዳንሰራ ማነቆ ሆኖብናል የሚሉት ሰለሞን፤ በተለይም ደግሞ ከሚዲያ እና ከተለያዩ ነገሮች እንድንጠፋ አድርጎናል ብለዋል፡፡

እንደዚሁም የተለያዩ ክልሎች ጋር እየሄድን ፅህፈት ቤቶችን ለመክፈት እንዳንችል አድርጎናልም ይላሉ፡፡ ምክንያቱም ፅህፈት ቤት ለመክፈት የሄድንባቸው አካባቢዎች ከምርጫ ቦርድ የተሰጣቹ ፈቃድ የታለ በማለት ይከለከሉናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ ፓርቲውን ለማጠናከሪያ ይውል የነበረውን የገቢ ማሰባሰቢያ እንዳናደርግ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ስለዚህ ‹‹አንድ ድርጀት ከአባላት የአቅም ማጠናከሪያ ለመሰብሰብ የሚያስችለው ሂደት ላይ ተፅዕኖ ካሳደረበት የለም ማለት ነው›› ብለዋል፡፡

የተነሳውን ቅሬታ እና ወቀሳ በሚመለከት ኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ሶልያና ሽመልስ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ የኮሮና ቫይረስን መግባት ተከትሎ ለከፍተኛ የሆነ የእንቅሰቃሴ ገደብ ነበር ሲሉ አስታውቀዋል።

ሶሊያና አያይዘውም ለየትኛውም ፓርቲ ኮቪድ ከገባ በኋላ ሰርተፍኬት አልሰጠንም ብለዋል፡፡ በፈረቃ እንደሚሰራ ያነሱት ሶልያና በሙሉ እንቅስቃሴውን ለማድረግ ብዙ ግድቦናል፡፡ ስለዚህም ከዚህ ቀደም እንደምንሰራው ሳይሆን ጊዜው ረዘም ሊል ይችላል ብለዋል፡፡

ኢህአፓ ለመጀመርያ ጊዜ ይፋ የሆነው እና ለመጀመርያ ጊዜ የመአከላዊ ኮሚቴ አባላትን ከመረጠ ነሃሴ 26 /1967 45 አመት የሞላው ሲሆን ቀደም ብሎ በሚያዚያ 1 ቀን 1964 ጀርመን በርሊን ላይ ‹‹የኢህአፓ ወላጅ ድርጅት›› የኢትዮጲያ ህዝባዊ አንድነት ( ኢህአድ) በኢትዮጲያ ገብቶ መዋቅሮችን ሲሰራ 3 ዓመታት ከአራት ወር ከፈጀበት በኋላ ኢህአፓ ተመስርቶ 45 ዓመት የሞላው፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com