በእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ጥያቄ እና የዐቃቤ ሕግ ተቃውሞ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

Views: 150

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት እነ  እስክንድር ነጋ በጠየቁት የዋስትና መብት እና የዐቃቤ ሕግ ምላሽ ላይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ።

እስክንድርን ጨምሮ ሰባት ሰዎች የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ እና በሽብር ወንጀል በዚህ ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በአካል ካልተገኙት 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች በስተቀር ሌሎቹ አምስቱ ተከሳሾች በአካል በችሎት ተገኝተው ክሱ ተነቦላቸዋል።
የክስ መነበብን ተከትሎ በአራት ጠበቆች የተወከሉት አምስቱ ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ለፈርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።
ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በተለይ  እስክንድር ነጋ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተከሰሱ በመሆኑ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 25 ዓመት የሚያስቀጣ በመሆኑና ድርጊቱም የሰው ህይወት የጠፋበት እና ከ187 ሚሊዮን ብር በላይ የወደመበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንዲሁም ሌሎቹ ተከሳሾችም በተመሳሳይ መልክ የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስት መብት ና የሚያስከለክል በመሆኑ ሕጉን በመጥቀስ ሕጉ የዋስትና መብትን ይከለክላል በማለት ተቃውሞ አቅርቧል።

ችሎቱ በዋስትና መብት ላይ የተነሳውን ክርክር የግራ ቀኙን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠትና የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ለመቀበል ለመስከከረም 12/2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com