የእለት ዜና

ራያ ዩንቨርስቲ የስንዴ ምርጥ ዘር እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ ነው

ራያ ዩንቨርስቲ በ6.3 ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ ምርጥ ዘር በመዝራት ከ180 ኩንታል በላይ ምርት በመሰብሰብ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ለሚያጋጥም የስንዴ ምርጥ ዘር ብዚት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ።

የስንዴ ምርጥ ዘር ብዚቱ ለማስፋፋት የዩንቨርስቲው የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ከሓድነት ራያ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን እና ስራው በዞኑ የሚያጋጥመዉን የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር ለመቅረፍም ድርሻው የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ዩንቨርስቲው ከአላማጣ ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር በ1.4 ሄክታር መሬት “ኑመን ቫራይቲ” የተሰኘ አዲስ የባቄላ ዘር እንዲሁም ከአፍሪካ ራይዝንግ ጋር በመተባበር “ዴሾ ግራስ” እና “ቁሉምሳ” የተሰኙ የከብቶች መኖ በማባዛት ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ እየሰራ መሆኑ ዩኒቨርስቲው ኣስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 98 መስከረም 9 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!