የእለት ዜና

አዲሱ የኢንቨስትመንት ደንብ ለአገረ ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ ዘርፎችን አሰፋ

አዲስ የጸደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 474/2012 ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን ከስምንት ወደ 30 ከፍ አድረጓል፡፡

አዲስ የጸደቀው የኢንቨስትመንት ደንብ ቀድሞ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ተከልለው የነበሩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከስምነት ወደ 30 ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለሉ ኢንቨስትመንት መስኮችን እንዲሁም ከመንግሰት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶችን በአዲስ መልክ አካቷልላ፡፡

በደንቡ አዲስ የተካተቱት ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የኢንቨስትመንት መስኮች በተለያዩ የብሔራዊ ዋና ዋና መስመሮች የኤሌክተሪክ ኃይል ማሰተላለፍ፣ ነዳጅ እና የነዳጅ ምርቶችን ማቅረብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመረተን የራስ ምርት በጅምላ መሽጥ እና ኤሌክትሪክ ንግድን ሳይጨምር የችርቻሮ ንግድ፣ ጥሬ ቡና፣ ጫት፣ የቅባት እህል፣ ጥራጥሬ፣ ማዕድናት፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የተፈጥሮ ደን ውጤቶች፣ ዶሮ፣ እና ጋማ ከብቶችን ጨምሮ ከብቶችን ከገበያ በመግዛት በመላክ የሚሰራ የውጭ ንግድ፣ ቡታጋዝና ቢቱመንን ሳይጨምር የገቢ ንግድ፣ የኮከብ ደረጃ ያላቸው ሳይጨምር የሆቴል፣ የሎጅ፣ የሪዞርት፣ የሞቴል፣ የእንግዳ ማረፊያ እና የፔንሲዮን አገልግሎት፣ የወጭ አገር ብሔራዊ ምግብ የሚቀርብ የኮከብ ደረጃ ያለው የሬስቶራንተ አገልግሎትን ሳይጨምር የሬስቶራንት፣ የሻይ ቤት፣ የቡና ቤት፣ የመጠጥ ቤት፣ የምሽት ክለብ እና ምግብ የማቅረብ አገልግሎት፣ ከደረጃ አንድ በታች የሆኑ የኮንስትራክሽን እና የቁፋሮ አገልግሎት እንደሆኑ በአዲሱ ደምብ ላይ ተገልጿል፡፡

እንዱሁም የጉዞ ወኪል፣ ጉዞ ትኬት ሽያጭ እና የንግድ ደጋፊ አገልግሎት፣ የማስጎብኘት አገልግሎት፣ ለተወሰኑ ኢንዱስትሪ የሚገለግሉ ከባድ መሣሪያዎችን እና ልዩ ተሸከርካራችን ሳይጨምር መሣሪያዎች፣ ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎችን ማከራየት፣ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡ የዳቦ እና የኬክ ምርቶች ማዘጋጀት፣ የወፍጮ ቤት አገልግሎት፣ የጸጉር ማስተካከል እና የቁንጅና ሳሎን አገልግሎት፣ የአንጥረኝነት ሥራ እና በአፍሪካ ደረጃ የማይካሄድ የልብስ ስፌት፣ የአውሮፕላኖች ጥገና እና ዕድሳትን ጨምሮ የጥገና እና የዕድሳት አገለግሎት ሆኖም የከፍተኛ ኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች እና የህክምና መሳሪያዎች ጥገና እናዕድሳት ሰሳይጨምር፣ በአውሮፕላን ማረፊያ ቦታ ለሚቆሙ አውሮፕላኖች የሚሰጡ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች፣ እንጨት የመሰንጠቅ ሥራ፣ የጣውላ ሥራ እና ያልተጠናቀቁ የእንጨት ውጤቶችን የመገጣጠም ሥራ፣ የግምሩክ አስተላላፊ አገልግሎት፣ ብሎኬት እና ጡብ ማምረት፣ የከባ ድንጋይ ማውጣት፣ የሎተሪ እና የሰፖርት ውርርድ ሥራዎች፣ በኢዱስትሪ መጠን የሚካሄዱትን ሳይጨምር የልብስ ንጽህና መስጫ አገልግሎት፣ የጥበቃ አገልግሎት፣ የድለላ ሥራዎች እና ከፍተኛ የዘርፍ ዕውቀት እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ልምድ እና የሥራ ትስስር የሚጠይቁ መርከቦችን እና ሌሎች ተመሳሳየው ሙያተኞችን ከሥራ ጋር የማገናኘት አገልግሎትን ሳይጨምር የግል ሥራ እነ ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት መሆናቸው በደንቡ ላይ ተቀምጧል፡፡

ደንቡ ላይ አዲስ ከተካተቱት ኢንቨስትመንት መስኮች ውስጥ የባቡር ትራንስፖርት፣ የኬብል መኪና ትራንስፖርት፣ የኮልድ ቼይን ትራንስፖርትን ሳይጨምር የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አንዱ ነው፡፡

ከዚህ በፊት “የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 270/2004” በሚለው ደንብ ላይ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ ዘርፎች የመገናኛ ብዙሀን ሥራዎች፣ የብሮድካስት ሥራዎች፣ የጥብቅናና የህግ አገልግሎት፣ አገር በቀል የባህል መድኃኒቶች ማዘጋጀት፣ የባንክ፣ ኢንሹራንስና አነስተኛ ብድርና ቁጠባ፣ እቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍና የመርከብ ውክልና አገልግሎት፣የማስታወቂያ እና የፕሮሞሽንና የትርጉም ሠራዎች ናቸው፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com