የመንግስት የልማት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አልሰበሰበም

Views: 66

የመንግስት የልማት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በየነ ገብረመስቀል የ2012 በጀት አፈፃፀምን አስመልክቶ በሰጡት መስከረም 20/2013  መግለጫ ላይ እንዳሉት ወደ ግል ይዞታ ከተዘዋወሩ ድርጅቶች አጠቃላይ የሽያጭ ገቢ መሰብሰብ የነበረበት 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቢሆንም መሰብሰብ የነበረበትን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ያህል ገቢ አለመሰብሰቡን አስታወቁ።
የተሰበሰበው የገንዘብ መጠንም በ2012 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ደግሞ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን በድምሩ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ነውም ብለዋል፡፡ ገቢው ላመሰብሰቡ እንደ ችግር ሆነ የተነሳውም ሂሳብ በመዝጋና በማስመርመር በኩል ወደ ኋላ የቀሩ ድርጅቶች መኖራቸው ተነስቷል፡፡

ኤጀንሲው በ2012 በጀት ዓመት 338 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 300 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከልማት ድርጅቶች በአጠቃላይ 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ትርፍ መገኘቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ምርትና አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሬ ከሚሸጡ ድርጅቶች 8 ነጥብ 67 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱንም የተናገሩት አቶ በየነ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ 3 ነጥብ 74 ቢሊየን ዶላር በማስገባት በአንደኝነት ደረጃ ላይ ሲገኝ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ደግሞ 3ነጥብ 43 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በማስገኘት የሁለተኝነት ደረጃን አግኝቷል ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከፕራይቬታይዜሽን ሽያጭ ቅድሚያ ክፍያ 1 ነጥብ 4 ቢየን ብር፣ ከፕራይቬታይዜሽን ውዝፍ ክፍያ ፣ 1 ነጥብ 8 ቢሊየንና ከፕራይቬታይዜሽን ሽያጭ በህግ ከተያዙ ውዝፍ ዕዳዎች 1 ቢሊየን ብር ገቢ ለማድረግ ለህግ የማቅረብና ውሳኔ ሲያገኙ የምስፈፀም እቅድ መያዙን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ወደ ግል ይዞታ ይዘዋወራሉ በሚል እቅድ ከተያዘላቸው የመንገስት ልማት ድርጅቶች መካከል በ2012 በጀት ዓመት አንድም ድርጅትን ወደ ግል ይዞታ አለመዘዋወሩን ከኤጀንሲው ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com